Connect with us

በአራት የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር ይተላለፋል

በአራት የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር ይተላለፋል
Photo Facebook

ዜና

በአራት የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር ይተላለፋል

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል: በአራት የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጸሎት እና የትምህርት መርሐ ግብር ይተላለፋል፤ ከነገ ጀምሮ በየምሽቱ ከ3፡00 እስከ 4፡00 ለአንድ ወር!

• ሰባቱ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል አብያተ እምነቶች በፈረቃ ይሳተፋሉ፤
• የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት፣ ከፌዴራል መንግሥት ጋራ መክሮ ያመቻቸው ነው፤

• ከነገ መጋቢት 28 ጀምሮ ለአንድ ወር፣ጸሎት እና የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት ይሰጣሉ፤
• የተንሰራፋውን ግለኝነት፣ ኢፍትሐዊነት፣ ኢሰብአዊነትና ርኵሰት እያወገዙም ያስተምራሉ፤
• ጤናማ እና ሰላማዊ ማኅበራዊ ግንኙነት፣መከባበር እና መተዛዘን እንዲጎለብት ይመክራሉ፤

ኢቴቪ፣ ፋና፣ ዋልታ እና አዲስ ቴቪ፥ መርሐ ግብሩ የሚተላልፋባቸው ጣቢያዎች ናቸው፤
ነገ በመክፈቻው፣ባለሥልጣናት ከቤተ መንግሥት በሚሳተፉበት መርሐ ግብር ይጀመራል፤

አብያተ እምነቶቹ፥ ለትምህርት መርሐ ግብሩ ብቁ መምህራን እንዲመድቡ ጽ/ቤቱ ጠየቀ፤
የክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤቶች፣ መርሐ ግብሮቹን በየቋንቋው ያስተባብራሉ፤
“በቫይረሱ ከቤተ እምነቱ የራቀውን ምእመን ልብ፥ ከፈጣሪው እንዳይርቅ ያግዛል”/ጽ/ቤቱ/

(ምንጭ:-ሐራ ተዋህዶ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top