Connect with us

“የሐጢያት ደመወዙ ሞት ነው”፤ ሞትማ ሲያንሰን ነው!!

“የሐጢያት ደመወዙ ሞት ነው”፤ ሞትማ ሲያንሰን ነው!!
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

“የሐጢያት ደመወዙ ሞት ነው”፤ ሞትማ ሲያንሰን ነው!!

“የሐጢያት ደመወዙ ሞት ነው”፤ ሞትማ ሲያንሰን ነው!! \ (ጫሊ በላይነህ በድሬቲዩብ )

እነሆ በኖብል ኮሮና ቫይረስ የተለከፉ ሕዝቦች ቁጥር አንድ ሚልየን ዘለለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በተለያየ ምክንያት ያልታወቀውን በመገመት ቁጥሩን በአስር እጥፍ ያደገ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ዛሬ እንደጣልያን ባሉ አገራት በ24 ሰአት እድሜ ከ800 በላይ ሰዎች መርገፋቸው ያስደነግጣል። ቫይረሱ በአራት ወር ዕድሜው ከ58 ሺ በላይ የአለም ሕዝብ ወደሞት ይዞ መንጎዱ ያሳስባል። ኃያሏ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የቫይረሱ ጠንካራ ምት ቀልቧን ገፏታል፤ አሸማቋታል።

እናም ብዙ ሰዎች አሁን አሁን የፈጣሪን መኖር እና በመዳፉ ላይ ስለመኖራችንም በደንብ ገብቷቸዋል። ብዙዎችም አልፈው ተርፈው ገዳዩን ቫይረስ የፈጣሪ ቁጣ ነው ብለዋል።

አዎ!.. ሐጢያታችንማ ፅዋው ሞልቶ ፈሷል። ለገባነው ቃልኪዳን የማንታመን ሴሰኛ ሆነናል። በወለዱን፣ ባሳደጉን ወላጆቻችን ላይ የምናምፅ ዋልጌዎች ሆነናል። በወንድም፣ በእህታችን ላይ የምናደባ ጨካኝና ከሀዲዎች ሆነናል። ጓደኞቻችን፣ ባልደረቦቻችንን ለመጣል እንቅልፍ አጥተን የምናድር አሳዛኝ ፍጡሮች ሆነናል። የሰው ላብ ቀምተን የምንበላ ጨካኝ ፍጡሮች ሆነናል። ፍቅር፣ ርህራሄ የራቀን ራስወዳድ ከሆንን ቆይተናል።

አዎ!.. የሐጢያችን ጥግ መድረሻው ሩቅ ነው። አዎ! የገዛ ወገናችን ላይ ቂምና ጥላቻ አስፋፍተናል። በዘር፣ በጎሳ፣ በሀይማኖት ተቧድነን “እኛን አይመስሉም” ያልናቸውን አጥቅተናል፣ ገድለናል፣ አሳደናል። ጥረው ግረው ያፈሩትን ቤትና ንብረት ዘርፈናል፤ አቃጥለንም እሳቱን ሞቀናል።

አዎ!…የእኛ ሐጢያትማ ፅዋው ሞልቶ ከፈሰሰ ቆይቷል። ሱሰኞች፣ ሰካራሞች ሆነናል። ለገንዘብና ጥቅማጥቅም አብዝተን ሰግደናል። ምድራዊ ሥልጣናችንን ተመክተን ከድሆች ቀምተናል። ቤተሰብ በትነናል። አረጋዊያንን ያለጧሪ፣ ሕጻናትን ያለአሳዳጊ ያስቀረን ጨካኞች ሆነናል።

አዎ!…ምድራዊ ሥልጣናችንን መከታ አድርገን በሕዝብ ገንዘብ ያለአግባብ በልጽገናል።ሰርቀን ባፈራነው ሐብት በአደባባይ እዩኝ እዩኝ አብዝተናል። የተቃወሙንን ገድለን፣ አስረን፣ አሳደን ስናበቃ ንፁህና የሕዝብ ተቆርቋሪ መስለን ደስኩረናል።
አዎ!…የእኛ ሐጢያትማ ውሀ ልኩን ማን አውቆት? ለእኔ ለእኔ ብቻ ማለት አብዝተናል። አካፍሎ መብላትን፣ የተቸገረ መርዳት፣ መደገፍን ከዘነጋን ሰንብተናል።

አዎ!…መፅሐፉም ለሐጢያት ደመወዙ ሞት ነው ይላል። በሞታችን አፋፍ ላይ ቆመን እንኳን የበደልነውን ብቻ ሳይሆን የበደሉንን ይቅር ብንል፣ ፍቅርን ብናስቀድም ፈጣሪ በታረቀን ነበር። ግን ችግሩ አሁንም ከስህተታችን፣ ከሐጢያታችን አለመማራችን ነው። ወደራሳችን መመልከት፣ ራሳችንን፣ አጥፊዎችን መገሰፅ አለመድፈራችን ነው። ለይቅርታ ዝቅ ማለት እንደውርደት ማየታችን ነው። ዉይ ሰዎች!..ምን አይነት ግብዝ ፍጡሮች ነን?!..

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top