Connect with us

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 ደረሰ

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 ደረሰ
Photo: Social media

ዜና

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 ደረሰ

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 ደረሰ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 89 ሰዎች ውስጥ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በመረጋገጡ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 38 እንደደረሰ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት፤ ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሦስቱም ግለሰቦች የውጭ አገሮች ጉዞ ታሪክ ያላቸውና ሁሉም በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው።

”የመጀመሪያው ግለሰብ የ29 ዓመት ወንድ ሲሆን መጋቢት 10 ቀን ከዱባይ የመጣና በበሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው ነው” ብለዋል።

ሁለተኛው የ34 ዓመት ወንድ መጋቢት 23 ከዱባይ የመጣና በማቆያ የነበረና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበረው መሆኑ ታውቋል።

ሶስተኛዋ የ35 ዓመት ሴት በመጋቢት 25 ከስውዲን የመጣችና በማቆያ የነበረች መሆኗን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ85 ዓመት ኢትዮጵያዊ አዛውንት አገግመዋል።

ዛሬ ከቫይረሱ ያገገሙትን የ85 አዛውንት ጨምሮ በድምሩ አራት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

#ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top