Connect with us

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እጅግ በሚያበረታታ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑ ተገለጸ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እጅግ በሚያበረታታ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑ ተገለጸ፤ አጠቃላይ የግንባታው ሂደትም 72.4 በመቶ ደርሷል፡፡
Photo Facebook

ዜና

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እጅግ በሚያበረታታ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑ ተገለጸ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እጅግ በሚያበረታታ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑ ተገለጸ፤ አጠቃላይ የግንባታው ሂደትም 72.4 በመቶ ደርሷል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እጅግ በሚያበረታታ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑን የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡ የሕዳሴው ግድብ የተጀመረበትን 9ኛ ዓመት በዓል አስመልክቶ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ለጋዜጠኞች በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አጠቃላይ የግንባታው ሂደትም 72.4 በመቶ መድረሱ ክቡር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

የ9 ዓመታት የግንባታ ጉዞ በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ውስብስብና አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱን ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ ምክንያቶቹም የግድቡ ግንባታ ውስብስብነትና የኮንትራት ሁኔታ እና ግድቡ የሚሠራው በድንበር ተሸጋሪ ትልቅ ወንዛችን ላይ በመሆኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከታችኞቹ ተፋሰስ ሀገሮች ላይ ስምምነት ላይ አለመደረሱ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የግድቡ ግንባታ የታቀደውን ለመከወን ከማያስችል የኮንትራት ውል ወጥቶ በጥሩና አበረታች አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡ የሲቪል ሥራው 86.6 በመቶ፣ የብረታ ብረት ሥራው 20.4 በመቶ፣ የተርባይንና የኃይል መቀበያና ማከፋፈል ሥራዎች 44.3 በመቶ በአጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ 72.4 በመቶ መድረሱን ጠቁመው አጠቃላይ ግንባታው በሁለት ሺፍት እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በመጪው ክረምት ውሃ የመያዝ ዕቅድም እንዳለ ጠቁመዋል፡፡

ከታችኞቹ ተፋሰስ አገሮች ጋር በተያያዘም በሦስቱ አገሮች መካከል የሚደረገውን ድርድር በቴክኒካዊ መፍትሄ መፍታት ሲቻል ጉዳዩ ፖለቲካዊ እና ዓለም አቀፍ ገጽታ እንዲኖረው የማድረግ ጥረት በተለይም በግብጽ መኩል መኖሩን ገልጸው በኢትዮጵያ በኩል መተማመንንና መልካም ጉርብትናን ለማጠናከር መርሆዎችን ተከትላ እየሠራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ የግል ሴክተሩና መንግሥት እጅግ በሚያበረታታ አፈጻጸም ላይ የሚገኘው ታላቁ ግድባችን

እስኪጠናቀቅ ድረስ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ቁርጠኝነት፤ በተናጠልም ሆነ በጋራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የግንባታው ሂደት እንዳይስተጓጎል የብሔራዊ ታክስ ፎርስና የሚመለከተታቸው ኮሚቴ አባላት ትኩረት ሰጥተው እየሠሩ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ምንጭ:- የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top