Connect with us

ጫት ቃሚዎች ኮሮናን እንዳይጋብዙ ተለመኑ…

ጫት ቃሚዎች ኮሮናን እንዳይጋብዙ ተለመኑ...
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

ጫት ቃሚዎች ኮሮናን እንዳይጋብዙ ተለመኑ…

ጫት ቃሚዎች ኮሮናን እንዳይጋብዙ ተለመኑ…

በአገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ ለኮሮና ቫይረስ በስፋት መስፋፋት የጫት ስርጭት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እና ህዝቡም እራሱን ከጫት እና ከመሰል ሱሶች እንዲያርቅ አንድ ምሁር አስጠነቀቁ።

ላለፉት ሃያ አመታት በጫት ስርጭት እና በሚያስከትላቸው የጤንነት እና ማህበራዊ ጉዳቶች ዙሪያ ሰፊ ምርምር ያካሄዱት ዶክተር ማዋርዲ አብዱላሂ በቅርቡ እንዳስታወቁት ጫት ኢትዮጵያ ውስጥ ማህበራዊና ባህላዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቶች ለጊዜ ማሳለፊያ፣ ከድብርት መላቀቂያ፣ ለጥናት ማጀቢያ በ ሚል ሰበብ በብዛት ስለሚቅሙት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ መሆኑን ተመራማሪው ጠቅሰው የጫት ተክል ከእርሻ እስከ ጉርሻ በብዙ ሰዎች እጅ ንክኪነት የሚተላለፍ በመሆኑ ለቫይረሱ በስፋት መስፋፋት ያለው አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ብለዋል።

የጫት ቅጠል በተፈጥሮው እንደሌሎች የሚበሉ አታክልቶች በአግባቡ የማይታጠብ፣ መጠቅለያው የኮባ ቅጠልም እንዲሁ በብዙዎች የ ሚተሻሽ፣ንፅህና የጎደለው በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ በከተማ ሆነ በገጠር የሚገኙ ወጣቶችን በቀላሉ ለማጥቃት ጫትን እንደ መንደርደሪያነት አንዳይጠቀመው በብዙዎች ዘንድ ተሰግቷል።

በጫት ዙሪያ ሰፊ ጥናት ያደረጉት ዶክተር ማዋርዲ እንዳብራሩት እና በ አንዳንድ መሰል ጥናቶችም እንደተገለፀው በኢትዮጵያ ውስጥ 16 ሚሊዮን ጫት ተጠቃሚዎች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ይህ ማለትም ከአጠቃላይ ህዝባችን ውስጥ 15% የሚጠጉት ጫት ቃሚዎች በመሆናቸው የበሽታውን ስርጭት ለ መግታት ሆነ ለ መቆጣጠር መንግስት እና ህዝቡ ጠንካራ፣የተቀናጀ እና የማያወላዳ እርምጃ መውሰድ አለበቸው ብለዋል።

ምንም እንኳን ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ህልውናቸው በ ጫት ስርጭት እና ሽያጭ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፣ ከጫት ሽያጭ በ ቀረጥ መልክ የሚሰበስበውም በ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ገንዘብ ለመንግስት ካዝና የሚገባ ቢሆንም፣ የዜጎች ድህንነትን መታደግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ብዙዎች ይመክራሉ።
( ኤልያስ አወቀ /ህብር ራዲዮ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top