Connect with us

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደረሰ

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደረሰ
Photo: Social media

ጤና

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደረሰ

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፈው 24 ሰአታት ውስጥ በ66 ሰዎች ላይ ባደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መኖራቸው መረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢንስቲትዩቱ ይህ መረጃ እስከ ተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ በአጠቃላይ 1013 የላቦራቶሪ ምርመራ አካሄዷል።

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ አምስት ደርሷል፡፡

በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሁለት ግለሰቦች የ30 ዓመትና የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ በተመሳሳይ በረራ ከዱባይ በመጋቢት 15፣ 2012 ዓ.ም ወደ ሀገር የገቡ ናቸው ተብሏል።

ግለሰቦቹ በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ሶስተኛዋ ታማሚ የ60 ዓመት ዔድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 6፣2012 ዓ.ም ከፈረንሳይ የተመለሱ እና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ የበሽታውን ምልክት በማሳየታቸው በለይቶ ማቆያ ውስጥ የቆዩ ናቸው።

ሶስቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑም ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ አንድ ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ሁለት ታማሚዎች ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን ሁለት ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡ ያገገሙት ታማሚዎቹ ለጥንቃቄ ሲባል በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

እስከ ትላንትናው ዕለት ድረስ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱ ቢነገርም መጋቢት 18 ኮሮና ቫይረስ ተገኘባት ተብላ የነበረችው ታካሚ በተደረገላት ተደጋጋሚ ምርመራ ነፃ መሆኗ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ስለዚህ በዛሬው ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው የተነገረውን ሶስት ሰዎችን ጨምሮ በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 መሆኑ ታውቋል።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top