Connect with us

ጥሩ ከንቲባ ሲገኝ ጥሩ ነዋሪ መኾን ነው

ጥሩ ከንቲባ ሲገኝ ጥሩ ነዋሪ መኾን ነው
Photo Facebook

ጤና

ጥሩ ከንቲባ ሲገኝ ጥሩ ነዋሪ መኾን ነው

ከንቲባዬ ኾይ እርስዎም መልካም ማድረግ አይደክምዎ፤ እኔም ማመስገኔን አላቆም፡፡ ጎዳና ያዋለዎት ችግር ተቀርፎ ለደስታው አደባባይ ዳግም ያገናኘን፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

አዲስ አበባ ታድላለች፤ ቢያንስ ሃሰቡን ጥሎ የማይተኛ ከንቲባ አላት፡፡ ከንቲባው ግን የታደሉ አይመስሉኝም ቢያንስ እጅህን ታጠብ፣ ቤትህ ግባ፣ ራስህን አድን ሲባል የሚያላግጥ ብዙ ነዋሪ መሪ ናቸውና፤

ዛሬ ከንቲባዬ ጎዳና ዋሉ፡፡ አደባባይ እየዞሩ አምልጥ ሲሉ ቀሰቀሱ፤ ከማምለጥ ማልመጥ የሚቀናው ለዚህ አይነቱ ተግባር ምን ምላሽ እንዳለው መገመት አያዳግትም፡፡ የሚበጀው ግን ጥሩ ከንቲባ ሲገኝ ጥሩ ነዋሪ መሆን ነው፡፡

ብዙ መንግስት ሰራተኛ የምሽቷን ድራፍት ቤት ቀን በሞላባት ከተማ የተረፈውን ይዤ ከተማዬን እመራለሁ ያላለ ሹም ጎዳና ወጥቶ ታጠቡ፣ ተራራቁ፣ ግድ ካልሆነ ከቤት አትውጡ፣ ወገንን እርዱ ሲል ማየት መልካም ነው ተባረክ ያስብላል፡፡ ይሄንን ለማለት ሙሉ ሰው መሆን በቂ ነው፡፡

ጥሩ ነዋሪ ስለመሆን እያሰብኩ ነው፡፡ ከተማዬ መቅበር አትፈልግም፤ ከተማዬ ድንኳን መጣል አትሻም፤ ከተማዬ ወረርሽኙን ድል ማድረግ ናፍቃለች፡፡ እኔ ዝመት አልተባልኩም፤ የተባልኩት ቤትህ ተቀመጥ ነው፡፡ የተባልኩት አካላዊ ንክኪህን አስወግድ ነው፤ የታባልኩት ታጠብ ነው፡፡

ከብዙ አመት በኋላ አዲስ አበባ ታጠቡ እያለ አደባባይ የሚቀሰቅስ መሪ ነበራት የሚለው ግሩም ታሪክ ኾኖ በልጆቻችን ይፈተልበታል፡፡ የሚገርመው አልታጠብም ብሎ ታጠብ በሚለው መሪ ሙድ የሚይዝ ነበር የሚለውን ግን ማንም አያምንም፡፡

ኢንጅነሩ ከንቲባዬ መልካም ነገር መስራት አይደክማቸውም፡፡ እኔም ያው ማመስገኔን አልተውም፡፡ እንዲህ የኔና የነዋሪው ነገር በዚህ ደረጃ ሲገዳቸው፣ በዚህ ደረጃ እንቅልፍ አልባ ክራሞት ሲሰነብቱ ምን እላለሁ? አንድ ቃል ነው ያለኝ፤ ከንቲባዬ አመሰግናለሁ፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top