Connect with us

የአምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

የአምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ
Photo Facebook

ዜና

የአምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

አምባሳደሮች ምደብ ቦታ ይፋ ተደረገ

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዚሁ መሰረት አምባሳደሮቹ የሚመደቡባቸው አገራት ከዚህ በሚከተለው መሰረት ተወስኗል።

ባለሙሉስልጣን አምባሳደሮች
=======================
1. አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ አውስትራሊያ ካንቤራ
2. አምባሳደር ያለም ፀጋይ ኩባ ሃቫና
3. አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ቤልጄም ብራሰልስ
4. አምባሳደር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ግብጽ ካይሮ
5. አምባሳደር ባጫ ጊና ሞሮኮ ራባት
6. አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሱዳን ካርቱም
7. አምባሳደር ምህረታብ ሙሉጌታ ኤርትራ አስመራ
8. አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አልጀሪያ አልጀርስ እንዲሁም
9. አምባሳደር ተፈሪ መለስ እንግሊዝ ለንደን እንዲሰሩ ተመድበዋል። እንዲሁም

አምባሳደሮች
============
1. አምባሳደር አድጎ አምሳያ ስዊድን ስቶክሆልም ምክትል ሚሲዮን መሪ
2. አምባሳደር ጀማል በከር ባህሬን ማናማ ቆንስል ጄኔራል
3. አምባሳደር አብዱ ያሲን ሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ቆንስል ጄኔራል
4. አምባሳደር ለገሠ ገረመው ካናዳ ኦታዋ ምክትል ሚሰዮን መሪ
5. አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማርያም የተባበሩት አረብ ኢሚሪቶች ዱባይ ቆንስል ጄኔራል
6. አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አሜሪካ ሚኒሶታ ቆንስል ጄኔራል እንዲሰሩ ተመድበዋል።

አምባሳደሮቹ በተመደቡባቸው አገራት የፕሮቶኮል አሰራር መሰረት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ በቅርቡ ወደ ምድብ ቦታቸው ተንቀሳቅሰው ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ ይሆናል።

Source: Spokesperson Office of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top