Connect with us

ብልፅግና የህወሓትን የንብረት አካፍሉኝ ጥያቄ አጣጣለ

ብልፅግና የህወሓትን የንብረት አካፍሉኝ ጥያቄ አጣጣለ
Photo Facebook

ዜና

ብልፅግና የህወሓትን የንብረት አካፍሉኝ ጥያቄ አጣጣለ

የብልፅግና ፓርቲ ያካሄደው ውህደት ህጋዊና በአብላጫ ድምፅ ድጋፍ ያገኘ በመሆኑ ህወሓት ሊያቀርብ የሚችለው የሐብት መካፈል ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው አቶ አወሉ አብዲ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አስታወቁ።

አዲስ ዘመን ጋዜጣ አቶ አወሉን ጠቅሶ በዛሬው ዕትሙ እንዳስነበበው ህወሓት ከውህደቱ ካፈነገጠ በሀላ ብልፅግና ፓርቲ በአብላጫ ድምፅ ኢህአዴግ የሚባለውን ፓርቲ ማፍረሱን፤ ይህ ውሳኔ ደግሞ በህጉ መሰረት የግንባሩን ሐብት ወደተዋሀደው ፓርቲ አስተላልፎታል። “ኢህአዴግ የሚባል ፓርቲ ፈርሷል፣ በምትኩም የብልፅግና ፓርቲ ስለተቋቋመ ህወሓት ከማዕከል የሚካፈለው ምንም አይነት ንብረት የለም” ብለዋል አቶ አወሉ።

ህወሓት ክልሉ ላይ ያለው ሐብት ካለ ግን እሱን ይዞ ሊቀጥል እንደሚችል አቶ አወሉ ተናግረዋል።

የኢህአዴግን መፍረስ ተከትሎ ስለንብረት ክፍፍል ጉዳይ ህወሓት ከወራት በፊት ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ቦርዱም ጉዳዩን መርምሮ ህወሓት 25 በመቶ ድርሻ እንዳለው በመወሰን፤ የድርሻውን እንዲካፈልና ሒደቱም በስድስት ወራት እንዲጠናቀቅ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

አቶ አወሉ ምርጫ ቦርድ ስለሐብት ክፍፍል የሰጠውን ውሳኔ የብልፅግና ፓርቲ እንደማይቀበለው በደብዳቤ ማሳወቁን አስታውሰዋል።

ኢህአዴግ ከ5 ሚልየን በላይ አባላቱ በመዋጮ መልክ የሚያሰባስበው ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ ያለው ሲሆን በአዲስአበባ እና በክልል ከተሞች ህንፃዎች፣ ቢሮዎች ከምንም በላይ ደግሞ ኢንደውመንት የሚባሉ በቢልየን ብር የሚገመት ሐብት ያከማቹ ኩባንያዎች ያሉት መሆኑ ይታወቃል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top