Connect with us

“ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው አስበው ነበር” – ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን፣ማድሪድ

"ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው አስበው ነበር" - ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን፣ማድሪድ
Photo Facebook

ጤና

“ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው አስበው ነበር” – ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን፣ማድሪድ

“ብዙ ሀገሮችም ልዩ ነን ብለው አስበው ነበር” – ዶ/ር ኪሩቤል ተስፋዬ ከስፔን፣ማድሪድ

የኢትዮጵያንም የስፔንንም የጤና አቅም በቅርበት እንደሚያዉቅ ባለሙያ ሰሞኑን የታዘብኩትን ላጋራቹ። የ ዛሬ ሳምንት ድረስ ምንም እንኳ መንግስት ነዋሪዉ እንዲጠነቀቅ ቢናገርም የሚሰማ ሰው አልነበረም ፤ የ ኳስ ጨዋታዎች በየከተማው ነበሩ ፤ ስብሰባዎች ነበሩ፤ዮኒቨርሲቲዎች ክፍት ነበሩ፤ የሚሰማ ሰው አልነበረም ።

ህዝቡ ከቻይና አልተማረም ፤ ጎረቤት ካለችው ጣልያንም አልተማረም። የሚይዘው አልመሰለውም ፣እራሱን ልዮ አድርጎ የሚያድነው የመሰለውን ምክንያት ደረደረ።

አሁን ሀገሪቷ ከተዘጋጋች ቀናቶች ተቆጠሩ መውጣት የሚቻለው ምግብ ወይ መዳኒት ለመግዛት ነው፤ የ አንቡላንስ ድምፅ በየቦታው ነው፤ ሰው በየቦታው እየሞተ ነው። ፈርተናል ፣ ፈርቻለው ፤ ያስፈራል።

ሀገሬም ተመሳሳይ መንገድ መከተሏ ያስጨንቃል፤ ኢትዮጵያውም እስካሁን ምክንያት መደርደራችንን ቀጥለናል። መጀመሪያ ቻይና ሀይማኖት ስለሌላት ተቀጣች አልን ፤ ከዛ ጣልያን እና ኢራንን ሲያስጨንቅ እኛ ሀገር ሙቀት ስለሆነ አይገባም ማለት ጀመርን ፣ ብራዚል እና አውስትራሊያ ገብቶ አየን ከዛም ሀገራችን ገብቶ አየን።

አሁንም ከተያዙት ብዙሀኑ ነጮች ናቸው ኢትዮጵያውያንን አይዝም የሚል ምክንያት ሰማን። ከ 4 ቀን በፊት ሁለት ኢትዮጵያውያን ጣልያን ውስጥ ሞቱ። ድንገት እዛ ስለኖሩ ነው የሞቱት የሚል ስለማይጠፉ ከሟቾች አንደኛዋ ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ የሄዱ ነበሩ።

እስከመቼ ልዩ እንደሆንን እንዲሰማን ምክንያት እንደረድራለን? ፈጣሪ ልዮ አድርጎ የመጠንቀቂያ ጊዜ ሰቶናል እንጠንቀቅ።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top