Connect with us

የጠ/ሚ ዶ/ር ዓቢይ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች

የጠ/ሚ ዶ/ር ዓቢይ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች
Photo : Facebook

ዜና

የጠ/ሚ ዶ/ር ዓቢይ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች

ጠ/ሚሩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡ ከውይይታቸው በኋላም ኮሚቴው የተስማማባቸውን የውሳኔ ሃሳቦች አቅርበዋል፡፡

ዋና ዋና ነጥቦችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

•ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ማንኛውም ዜጋ ከበሽታው ነጻ መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በለይቶ ማቆያ እንቆይ ይደረጋል፤ለዚህም መለስተኛ ቦታዎችና ሆቴሎች እየተዘጋጁ ነው፡፡

•የዚህ ሙሉ ወጪም በሆቴሎቹ በሚቆዩ ግለሰቦች የሚሸፈን ይሆናል፡፡

•የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከ30 በላይ ሀገራት በረራውን እንዲያቋርጥ ተወስኗል፡፡

•ከእምነት ተቋማት አንጻርም ሰዎች የሚሰባሰቡባቸውንና ንክኪ የሚፈጠርባቸውን ቦታዎች ለመቀነስ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተደርጓል፤ የእምነት አባቶቹም ዝርዘር ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ ይሰጣሉ፡፡

•ከማረሚያ ቤቶች ጋር በተያያዘም ተጨማሪ ቦታ ማዘጋጀት፣ አዳዲስ ታራሚዎች የሚገቡ ከሆነ ከበሽታው ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የቤተሰብ ጥየቃ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ማድረግ፣ ህጻናት የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ፣ ጉዳያቸው ቀላል የሆኑ ሰዎችም እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡

•የዓለም ባንክ ደግሞ በሽታውን ለመከላከሉ ሥራ ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማገዝ ቃል ገብቷል፡፡

•በአዲስ አበባ የሚገኙ የምሽት መዝናኛ ቤቶችም ጥግግት ስለሚበዛባቸውና ለበሸታው አጋላጭ ስለሚሆኑ ከዛሬ መጋቢት 11/2012 ጀምሮ እንዲዘጉ ተወስኗል፡፡

•ክልሎች ላይ በሽታውን ለመመርመርና ድንገት በሽታው ቢከሰት ጥንቃቄ የሚደረግበት ሁኔታ ላይ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

•ሰዎች ከመጠንቀቅ ይልቅ አሁን ቸልተኝነት እያሳዩ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

•የውጭ ሀገራት ዜጎ በበሽታው ተይዘዋል በሚል ጥርጣሬ የሚደርሱ ማዋከቦች ተገቢ ባለመሆናቸው፣ በሽታውም ዘር፣ ቀለም፣ ኃይማኖት የማይለይ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ ማዋከቡ መቆም እንዳለበት ዶክተር ዐብይ አስገንዝበዋል፡፡

(አማራ መገናኛ ብዙሀን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top