Connect with us

ዳሸን ቢራ የጣዕም መጓደል እንዳጋጠመው አመነ

ዳሸን ቢራ የጣዕም መጓደል እንዳጋጠመው አመነ
Photo: Facebook

ዜና

ዳሸን ቢራ የጣዕም መጓደል እንዳጋጠመው አመነ

ከቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል ጋር በተያያዘ ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የተሰጠ መግለጫ

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ላለፉት 20 ዓመት ኢትዮጵያዊያን ደንበኞቹን ስኬታማ በሆነ መንገድ ሲያገለግል የቆየ ፋብሪካ ሲሁን በኢትዮጰያ በጥራቱ ተመራጭ ቢራ በመሆን በበርካቶች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ፋብሪካው የሚያመርተው የዳሽን ቢራ ምርት በአብዛኛው ከኢትዮጵያውያን አርሶአደሮች በሚገኝ ግብዓት ሙሉ በሙሉ (100%) ከገብስ ብቅል የጀርመንን የቢራ ጠመቃ መስፈርትን በማሟላት የሚጠመቅ ቢራ ነው፡፡

ፋብሪካው ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ በዓለም በቢራ ጠመቃ ቴክኖሎጂ ቁጥር አንድ የተባለለት ፋብሪካ በደብረብርሃን ከተማ የገነባ ሲሆን በጎንደር የሚገነኘውን ነባሩን ፋብሪካውን ደግሞ በማስፋፋትና አቅሙን በማዘመን ላይ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ከቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል ጋር በተያዘ ከተለያዩ አካላት ቅሬታዎች የደረሱን በመሆኑ በአፋጣኝ ችግሩን በመለየት እርምጃ ለመውሰድ የተንቀሳቀስን ሲሆን የደረሱን ቅሬዎችም ከተለመደው የቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል ጋር የተያያዙ እንጂ በሰው ጤና ላይ ምንም አይነት ጉዳት መጣ የሚል አልነበረም፡፡

የቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል አጋጣማቸው የተባሉ ምርቶችት ጀርመን ሀገር በርሊን ወደሚገኘው VLB የሚባል ዓለም ዓቀፍ የቢራ ጠመቃ ምርምርና ጥናት ማዕከል በመላክ የናሙና ምርመራ አድርገናል፡፡ በውጤቱም ምንም አይነት ለሰውልጅ የጤና ጉዳት የማያሰከትል ምርት መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ ይህም በኢትዩጵያ የምግብ ፣ የመዳኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባላስልጣን በድጋሚ የተረጋገጠ ሆኗል፡፡

በተቋማችንም ባደረግነው ማጣራት ከፋብሪካችን ምርት ውስጥ የቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል ደርሶባቸዋል ተብለው የተለዩት ምርቶቻችን አልፎ አልፎ የተከሰተ እና ከ0.05% የማይበልጥ ድርሻ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን አረጋግጠናል፡፡

ምርታችን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚሰራጭ እንደመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በመላው ሀገሪቱ ያሉ እና የቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል ያለባቸውን ምርቶች በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን፡፡

የፋብሪካችን የቢራ ጠመቃ ባለሙያዎች ከተላያዩ አለማቀፍ የቢራ ጠመቃ ጥራት መቆጣተሪያ መሳሪያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ችግሮችን መርምረው በመደርስ ማስካከያ እንዲደረግበት ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ችግሩ ዳግም እንዳይፈጠር ተጨማሪ የጥራት ቁጥጥር ስርዓት ዘርግተን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን ከኢትዩጵያ የምግብ ፣ የመዳኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ዳግም ናሙና በመውሰድ እና ገለልተኛ ምርመራ በማድረግ ቢራው የጥረት ደረጃው የጠመቀና ለደንበኛ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ስለሆነም በዚህ አጋጠያሚ የቢራ ጣምዕና ይዘት መጓደል ያለበት ምርት ላጋጠማችሁ ደንበኞቻችን በሙሉ ከልብ የመነጨ ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ በኋላ ፋብሪካችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በጥራ ላይ ፈጽሞ የማይደራደር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top