Connect with us

“ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአስቸኳይጊዜአዋጅ ልታውጅ ትችላለች” የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

"ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአስቸኳይጊዜአዋጅ ልታውጅ ትችላለች" የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Photo: Facebook

ጤና

“ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአስቸኳይጊዜአዋጅ ልታውጅ ትችላለች” የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ በተለያዩ ተቋማት እየተሰሩ ያሉ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በቂ አለመሆናቸውንም ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የአለም አቀፍ ጤና ደንብ የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶክተር ፈይሳ ረጋሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ሁሉም ተቋማት ያገባኛል በሚል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ሳይጠበቁ የቫይረሱን መከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው ብለዋል።

በተለይ የትምህርት፤ንግድ ፤ትራንስፖርት፣ ውሃ እና የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከታችኛው መዋቅራቸው ድረስ ወርደው በኃላፊነት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

“እያንዳንዱ ግንዛቤ መፍጠር አለበት በስሩ ያሉትን ተቋማት ሁሉ መድረስ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ይህ በፌደራል ብቻ ሳይሆን በክልሉችም ፤በዞኑችም በወረዳዎችም መድረስና ማጠናከር ያሰፈልጋል ብለዋል ዶክተር ፈይሳ።

በሀገሪቱ ከበሽታው ጋር በተገናኘ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተ ላነሳንላቸው ጥያቄ አቶ ፈይሳ ሲመልሱ ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ አከባቢዎች ትምህርት ቤቶች፤የሀይማኖት ስፍራዎች፤የትራንስፖርት ፤የስፖርት እንዲሁም የኢንድስትሪ ፖርኮች ተገቢ እና አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችና ስራዎች እየሰራን ነው ይላሉ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ቫይረሱ ከመግባቱ በፊት፣ከገባ በኋላ እና በመቀጠል የሚሰሩ ስራዎችን ለሚመለከታቸው ተቋማት አስታውቀናል ያሉት ዶክተር ፈይሳ አሁን ላይ ቫይረሱ አገር ቤት መግባቱን ተከትሎ በቀጣይ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ምክክር ጀምረናል ብለዋል።

ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የበለጠ አንዳይተላለፍ የሚወሰዱ እርምጃዎች አሉ የበለጠ የከፋና በማህበረሰብ ወረርሽኝ ሆኖ እንዳይከሰት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የቫይረሱ ስርጭት በከፋ ሁኔታ ከተስፋፋ ስራን ጨምሮ እንቅስቃሴች ሙሉ ለሙሉ እስከማገድም ይደረሳል የሚሉት ዶክተር ፈይሳ የባሰ አጣራጣሪ ነገር ካለ ግን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ማወጅ ይደረሳል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ግለሰብ ጋር ንኪኪ አላቸው በሚል የተጠረጠሩ 113 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ክፍል ገብተው ክትትል ሲደረግላቸው ነበር።

ከነዚህ ሰዎች መካከልም 74ቱ ላይ በተደረገ ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ ሆነው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መናገራቸው ይታወሳል።

ቀሪዎቹ 34 ሰዎች ደግሞ የምርመራ ውጤታቸው በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውንም ዶክተር ኤባ ተናግረዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው አምስት ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውንም ኢንስቲትዩቱ ተገልጿል።

በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቦታዎች በቫይረሱ ተጠርጥረው ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ ከገቡ ዜጎች መካከልም 1ሺህ 285 ሰዎች ከቫይረሱ ነጻ ተብለው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን ዶክተር ኤባ ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታትም 1 ሺህ 200 የህክምና ባለሙያዎችን ቀጥሮ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top