Connect with us

ሰበር ዜና ከኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጋር በተያያዘ

ሰበር ዜና ከኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጋር በተያያዘ

ዜና

ሰበር ዜና ከኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጋር በተያያዘ

ከኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ጋር በተያያዘ በሚቀጥሉት 15 ቀናት ትምህርት ቤቶች (ዩኒቨርሲቲዎችን አይጨምርም)፣ ስብሰባዎች፣ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲቆሙ፣ የሃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት መሰባሰብ እንዲቀንሱ መንግሥት መወሰኑን ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ሁሉም የመንግሥት ተሸከርካሪዎች ለሕዝብ የትራስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡ በርከት ያለ ትራንስፖርት ያላችሁ የግል ድርጅቶችየትራስፖርት አግልገሎት በመስጠት እንዲተባበሩ፣ መገናኛ ብዙሃን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ህብረተሰቡ ንጽህናውን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡ህብረተሰቡ ፍራቻን ቀንሶ በተረጋጋ ሁኖ ሥራውን እንዲከውን ያሳሰቡት ጠ/ሚ ዐብይ እስካሁን አምስት ሰዎች መያዛቸውንና ለሞት የሚያደርስ አደጋ አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ትላንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ማስተወቁ አይዘነጋም፡፡

ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ያለበት የመጀመሪያው ሰው ከተገኘ በኋላ ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች ሲከታተል መቆየቱን አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው 117 ሰዎች ተለይተው የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ቫይረሱን ለመለየት የሚያስችል ምርመራ ለማድረግ ከግለሰቦቹ ናሙና እየተወሰደ መሆኑ ተመላክቷል።

ምርመራ ከተደረገላቸው እና ከመጀመሪያው ተጠቂ ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ ከነበራቸው ሰዎች መካከልም ሶስት ግለሰቦች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

ከእነዚህ ውስጥም ሁለቱ የ44 እና የ47 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የጃፓን ዜጎች ሲሆን፥ አንደኛው ደግሞ የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ መሆኑ ታውቋል።

ሶስቱም ግለሰቦች በአዲስ አበባ ውስጥ የሚሰሩ እና ቫይረሱ ከተገኘበት የመጀመሪያው ግለሰብ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው መሆኑን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፥ ከተጠቂዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ስራ መጀመሩንም ጠቁሟል።።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top