Connect with us

የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ

የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ
AP Photo

ጤና

የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሪክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በሰጡት መግለጫ የኮሮና ቫይረስ “ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ” መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንድ በሽታ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሚባለው በዓለም ዙሪያ በተመሳሳይ ጊዜ በተለያዩ አገራት ውስጥ ሲሰራጭ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ እንዳሉት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከቻይና ውጪ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ13 እጥፍ ጨምሯል።


ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጨምረውም በሽታውን በተመለከተ እርምጃ ለመውሰድ የታየው ቸልተኝነት “በጣም እንዳሳሰባቸው” ተናግረዋል።

በቻይና ውሀን ግዛት የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በርካታ የአለም አገራትን በማዳረስ ከ4 ሺህ 380 በላይ ሰዎችን ሲገድል በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ደግሞ ከ122 ሺህ በላይ መድረሱን ተዘግቧል።(ጤና ሚኒስቴር)

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top