Connect with us

በግል የጥበቃ አገልግሎት ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ነው

በግል የጥበቃ አገልግሎት ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ነው

ህግና ስርዓት

በግል የጥበቃ አገልግሎት ላይ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ነው

በግል የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ዙሪያ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚረዳ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምክክር መድረኩ ዓላማ ሁሉም በመተባበር ሊሰራዉ በሚገባ ጉዳይ ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ ገልጸዋል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የልማት ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ እና እነኚህን የልማት ስራዎች ለማሳለጥ እና ዜጎች ከልማቱ ተቋዳሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ ለዚህ ደግሞ የፋይናንስ ተቋማት እና ባለ ሀብቶች በጋራ እየሰሩ እንዳለ ይታወቃል ብለዋል፡፡

በተጀመሩ የልማት እንቅስቃሴዎች የተገኙ በርካታ ዉጤቶችን አስተማማኝ ጥበቃ ልናደርግላቸዉ ይገባል ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ ከዉጭ ሀገር የመጡም ሆነ በሀገር ዉስጥ በኢንቬስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ያለምንም የደህንነት ስጋት እንዲሰሩ ንብረታቸዉ ሊጠበቅላቸዉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በምክክር መድረኩ በቀረበዉ አጭር ጥናታዊ ጽሑፍ በግል የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚስተዋሉ ችግሮች ተነስተዋል፡፡
በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለዉ በዚህ የምክክር መድረክ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች፣ የግል ጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡(ፌ/ፖሊስ ኮምሽን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top