Connect with us

ትንሿ ሀገር

"ትንሿ ሀገር"
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ትንሿ ሀገር

“ትንሿ ሀገር”
(አሥራት በጋሻው)

ግብጾች እስራኤልን በስሟ አይጠሯትም መጥራትም ነውር ነው። ”ትንሿ ሀገር ”ይሏታል። በስድስቱ ቀን ጦርነት የመጀመርያ ቀን
ሰኔ 5 ቀን 1967 (እ. ኤ. አ )የደረሰባቸውን ሽንፈት ሲያስታውሱ በልባቸው ስር የሚረጨው ቀጭን ቀዝቃዛ የደም ጥቅታ ይፍቃቸዋል።

በእስራኤል ሰአት አቆጣጠር ጥዋት አንድ ሰአት ከአስር ደቂቃ ላይ 16 ፈረንሳይ ሰራሽ የማጅስተር ፎጋ ጄቶች ሮኬት ታጥቀው ሀቶር ከሚገኘው የአየር ቤዝ ተነሱ ። የአቅጣጫ ፍሪኬውንሲ እያስተላለፉ በማስመሰል በረራ በተመሳሳይ መስመር ሲበሩ ታዩ። ከአራት ደቂቃ በኃላ እውነተኞቹ ተዋጊ ጄቶች ከዚያዉ የጦር ቤዝ ለቀቁ።

አንድ ሰአት ተኩል ላይ 200 ተዋጊ የጦር አውሮፕላኖች በምእራብ አቅጣጫ ወደ በሜዲትራኒያን ባህር ከራዳር እይታ ውጭ ዝቅ ብለው በረሩ። ከአንዱ በስተቀር 82 ቦታ የተተከሉ የግብጽ ራዳሮች ምንም መረጃ አልነበራቸውም። ርቀታቸውን ጨርሰው ወደ ግብጽ የአየር ክልል ተመለሱ። ከእጅ ምልክት ውጭ የእስራኤል የአየር ሀይል ፖይለቶች የሬድዮ መልእክት መለዋወጥ አልተፈቀደላቸውም ። የአውሮፕላን ብልሽት ቢያጋጥም እንኳ እርዳታ ከመጠየቅ ባህር ላይ እንዲከሰከሱ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል ።

የእስራኤል አባቶቻችን መንፈስ ያግዘናል። ግብጾች ደህንነታችንን: ነጻነታችንን እና የወደፊት ተስፋችን ከ1948 እና ከ1956 በኃላ ለሶስተኛ ጊዜ ተዳፍረዋል። ፖይለቶቹ በጠላት አየር ላይ እያጓሩ በመብረር መደምሰስ የጠላትን አስክሬን በርሀ ላይ በትኖ የእስራኤልን ህልውና ማረጋገጥ እና የታፈረች የተከበረች ሀገር ለትውልድ ማቆየት አላማቸው እንደሆነ በማሀላ አረጋግጠዋል ።

ግብጻውያን እስራኤላውያንን ከመናቅ ባለፈ ዝግጅታቸው ደካማ ነበር። ለሚጎች ለኢሎዝን እና ቶፖሎቭ ተዋጊ ጄቶች በአንድ አንድ ቤዝ ላይ ለጸሀይ አስጥተው ለጠላት አጋልጠው ለእስራኤል ጄቶች ተመቻችተዋል ። አውሮፕላኖቹ ከአሸዋ ምሽግ በስተቀር የሚጠብቃቸው የለም።የግብጽ ፖይለቶች ቁርስ ላይ ናቸው ።

ተዋጊ ጄት አደገኛና አጥፊ መሳሪያ ነው ። መሬት ላይ ተኝቶ ስታገኘው ግን ምንም አይደለም። የግብጽ ጥቂት የልምምድ አውሮፕላኖች አየር ላይ ነበሩ ። ጆርዳን ላይ የተተከለው ራዳር ከእስራኤል አቅጣጫ በድንገት የሚርመሰመሱ አውሮፕላኖች በስክሪን ላይ የተመለከተው ሰራተኛ በድንጋጤ ”ኢናብ ”ኢናብ’ሲል ተጣራ ።ግብጾች ለጦርነት የተለዋወጡትን ኮድ ከአንድ ቀን በፊት ቀይረው ለዚህ ሰራተኛ አልነገሩትም። ጬህቱን አልሰሙትም። ተርጓሚው ተኝቷል።

የግብጽ የመከላከያ ሚንስቴር ሚንስትር ማንም እንዳይቀሰቅሳቸው ተናግረው ከተኙ ጥቂት ደቂቃዎች አልፈዋል ። የመከላከያ ዋናው መስሪያ ቤት ዝግ ነበር ማለቱ ይቀለናል ።
ለእስራኤሎች ከዚህ የበለጠ አመቺ ጊዜ አያገኙም።

የግብፅ ሰማይ መከላከል አልቻለም ። 11 ኢላማ የነበሩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ የጦር አውሮፕላኖቻቸው የማይችሉት ቦንብ ወረደባቸው ። ከ20 እስከ 45 ደቂቃዎች ውስጥ በ90ኪግ ቦንብ ተደበደቡ ።

የማኮብኮቢያ ሜዳቸው ታረሰ ። 5ሜትር በ1ሜት ር ከስድሳ ሳንቲሜትር ርቀት ጉድጓድ ቆፈሩ። 86 አውሮፕላኖቻቸው ባሉበት ተሰነካክለው ቀሩ። ወደሙ።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት መጀመርያ የሰሙትን የውሸት የድል ዜና ተጣርቶ ሲመጣ ሽንፈትን መስማት አቅቷቸው ቤት ተቀምጠው ቀሩ።

የካይሮ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ይጨፍራል ። 161ጄቶት ጥለናል የሚል የሀሰት የድል ዜና በሬዲዬ ሲሰማ ህዝቡ ሰከረ።
የውርደታቸውን ዜና የወቅቱ አብራሪ የነበሩት ሰሞኑን የሞቱት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙባረክ በቅርብ በሰጡት ቃለ ምልልስ ንስሀ ገብተውበታል።

የስድስቱን ቀን ጦርነት የመዘገበው እና በ437 ገጽ የከተበው ሚካኤል ቢ ኦረን ለሁለተኛው ቀን ጦርነት ወደ ቤዛቸው የተመለሱት ከአደጋ የተረፋትን አውሮፕላኖችና አብራሪዎችን በመረጃ እየጠቀሰ ጽፎታል። ለግብጾች ዛሬም ”ትንሿ ሀገር” ናት።

ግብጽ የአባይን ወንዝ ታሪካዊ መብት አለኝ ስትል ያለእፍረት ስትናገር ተፈጥሮአዊ መብት ላላት ኢትዬጲያ ያላትን ንቀት ያሳያል።
መልካም የሳምንት መጨረሻ እስቲ ጀግናው የሀገሬ ሰው ሞባይል ላይ
8100 እንገናኝ ።
ቻው

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top