Connect with us

በትዳር ሕይወት የሚታቀፍ ሰው እንጂ ብሔር የለም

በትዳር ሕይወት የሚታቀፍ ሰው እንጂ ብሔር የለም
Photo: Facebook

ፓለቲካ

በትዳር ሕይወት የሚታቀፍ ሰው እንጂ ብሔር የለም

በትዳር ሕይወት የሚታቀፍ ሰው እንጂ ብሔር የለም፤ የሚሳመው ከንፈር እንጂ ብሔር አይደለም፤ ሴት እንጂ ብሔር ሚስት አይሆንም፡፡ ህዝብ የማነቅ ጥግ የሚያገባውን ልምረጥልህ እስከማለት ያደርሰሃል፡፡
***
ከስናፍቅሽ አዲስ
ከኮሮና ይልቅ ለዓለም የሚያሰጋው ይህ ዘረኛ ቫይረስ ነው ብሎ አንዱ እዚሁ መንደር ጽፎ አነበብኩ፤ እውነት ነው፡፡ ይሄ ቫይረስ የሆነ ንግግር ዓለም ቢያደምጠው ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ በረራዎች ይሰረዙ ነበር፡፡ የተባበሩት መንግስታት ኢቮሎሽንኑ ያልጨረሰ ፍጡር ከሰው ጋር ተቀላቅሏል ብሎ ይመክር ነበር፤ እንኳን እኛ በምንሰማው ቋንቋ እኛው ጋር ቀረ፤

የሴትየዋ ንግግር የፓርቲዋ፣ የተናገረችበት ቴሌቨዥን ጣቢያና የመሰል ቫይረሶች ሀሳብ ነው፡፡ አፈትልኮ ሳይሆን ከተሳካ ተሞክሮ የተባለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አክራሪ ብሔርተኞች በምትጠጣው ቢራ በምትበላው ምግብ ምርጫችን ተለማምደው አሁን በስኬት ወደ ትዳር አጋራችን ምርጫ ገብተዋል፡፡ ለእኔ ባል የምትመርጥልኝ የብሔሬ አክራሪ ለመሆን በቅታለች፡፡ ይሄ በኢትዮጵያ ምድር አፈር የሚገባ ሀሳብ ነው፤ ከንቱ ሀሳብ፡፡

አስቀድሞ ብሔር በትዳር ሕይወት አይታቀፍም፤ ሰው ሰው እንጂ ብሔር አያገባም፤ ብሄር ቅርጽ የለውም፤ ሲስቅም ደስ አይልም፤ ደም ግባት የሌለው ግዑዝ ነው፡፡ ከብሔርም አይወለድም፡፡ ብሔር ምንም የሆነ የአቅመ ቢሶች ጎራ ነው፡፡ በራሷ መልክ የማትተማመን ለቋንቋዬ ስትል አግባኝ ትላለች፤ በራሴ ሴትነት ክብር የሌላት ብሔርን አክብረህ አግባኝ ብላ ትጠይቃለች፡፡ በራሷ ስብዕናና ውስጣዊ ውበት የማትመካ ብሔሯን ጋሻ አድርጋ ትመጣለች፡፡ ግን እኔ ሴት ነኝ፤ ብሔር አላገባም ወንድ እንጂ፤ ኢትዮጵያዊ ወንድ ሴት እንጂ ብሔር አያገባም፡፡

ብሔር ከንፈር የለውም አይሳምም፤ የሚሳመው ውበት የሚሳመው ፍቅር የሚሳመው የሚወደድ ሰው ነው፡፡ ቫይረስ የሆነ ዘረኛ አስተሳሰብ ለቋንቋዬ ስትል አግባኝ የሚል ሀሳብ ይዞ አደባባይ ይወጣል፡፡ ይሄ ከኮሮና የሚከፋ የዓለም ቀፋፊ የዚህ ዘመን በሽታ ነው፡፡ ይሄ ህዝብን እንደ ዶሮ እንደ ጫጩት ማየት ነው፡፡ ምን እመራዋለሁ ቢሉት ህዝብን የትዳር አጋር ልምረጥልህ አይሉትም፤ እንዲህ ማድረግ የሚቻለው ለእንስሳ ነው፡፡ ለዶሮ ነው እንጂ ማስታቀፍ ሰው መርጦ የሚያቅፍ ፍጡር ነው፡፡

በብሔርተኝነት ሀሳብ ህዝብ ሌላውን ማግባት ከሌላው ጋር መሆን አንዱ የመስፋፋት ስልት ነበር፤ ኦሮሞ ደግሞ አቃፊ ነው፤ ብዙ ስርዓቶቹ የማካተት እንጂ የመለየት አይደሉም፤ አይሁድም ዓለምም ከሌላው ጋር መጋባትን እንደ መኖር ዋስትና ያየዋል፤ ሳይንስም እርስ በእርስ ከመጋባት ከሌላ ጂንና ዘር ጋር መቀላቀልን እንደ ጤንነት ይመለከተዋል፤ ለጤናማ አስተዳደርግ ልኬት አድርጎ ያየዋል፤ ዘረኝነት ግን ሊያውም ይህ አይነት ኮሮና ነው፤ ምንም ማየት የማይችል፤

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top