Connect with us

የአባይ ግድብ የሁላችንም ጉዳይ ነው!

የአባይ ግድብ የሁላችንም ጉዳይ ነው!
Photo: Facebook

ፓለቲካ

የአባይ ግድብ የሁላችንም ጉዳይ ነው!

የአባይ ግድብ የሁላችንም ጉዳይ ነው!

(ፍሬህይወት ሣሙኤል)
የኢትየጵያ መንግስት በአባይ ጉዳይ አሁን ያሳየውን ጠንካራ አቋም ከጅምሩም የነበረው መሆኑ ለሁለችን ትልቅ ኩራት ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የደወሉትንም ስልክ በሚመለከት በወቅቱ በአካል እዚያው ከነበሩ ሰዎች ከራሳቸው በግል እንደሰማሁት ጠቅላይ ሚ/ሩ ለዶናልድ ትራምፕ የስልክ ጥሪ እንዳልተለሳለሱላቸው ነበር። ጠቅላይ ሚ/ሩ በጊዜ ጠንከር ያለ መልስ መስጠታቸው የጉዳዩን ከባድነት ለፕሬዝዳንቱ ሳያስገነዝባቸው የቀረ አይመስለኝም።

እንዲሁም ከሁለት ሳምንት በፊት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ ታገሰ ጫፎ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤትና፤ ለሗይት ሃወስ የፕሬዝደንቱ የስራ ባልደረቦችና ለኮንግረስ ሴኔተሮች የኢትዮጵያ ፓርላማ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሊያደርገው እንደሚችል በመግለፃቸው ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ይህ አይነት ውይይቶችና ያለማቋረጥ የማስረዳት ተግባር መቀጠል ያለበት ነው።መቢቻል አንድ የዲፒሎማቶች ግብራሃይል ዲስ ላይ መጥቶ(ተቋቁሞ) በአሜሪካን ገንዘብ አሜሪካኖችን ቢያግባባልንም ጥሩ ነው።

ግብፆች በዚህ ሁለት አመት ውስጥ ከአባይ አንፃር ተስፋ ካደረጉዋቸው ጉዳዮች በሁለቱ ሳይሳካላቸው የቀረ ይመስላል። አንደኛው በተለይም የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች የማዕከላዊውን መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠሩ ኢትዮጵያን አፍርሰው ይገላግሉናል ቢለው ቢቋምጡም የኦሮሞ ፖለቲከኞች ግን አንፃራዊ የሃይል ሚዛን እጃቸው ከገባ በሗላ የኢትዮጵያን አንድነት በሚመለከት ያሳዩት ትልቅ የሀላፊነት ስሜት የግብፆችን ስሌት ለጊዜው አጨናግፏል (ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ውስጥ በአንድ ወቅት ከግብፅ በቀጥታ ፤ሌላ ጊዜ ደግሞ በሶስተኛ ወገን በኩል ሲደጎሙና ሲረዱ የነበሩ አክራሪ ብሄርተኞች ሃገር ቤት ገብተው “እንገንጠል ያልነው ለታክቲክ ነበር እንጅ ከኛ ወዲያ ኢትዮጵያዊ ማን ነው” ማለት መጀመራቸው ግብፆችን አመድ አፋሽ አድርጓቸዋል)።

በዚሁ አጋጣሚ የሚያሳስበኝ ግብፆች በቀድሞ ወዳጆቹ በኩል ያልተሳካላቸውን የኢትዮጵያውያን የእልቂትና የብተና አጀንዳን በኦሮሞዎቹ መሃል በኦሮሚያ ለኩሶ እርስ በርስ እንዲያገዳድሏቸው ኦሮሞዎች ይፈቅዱ ይሆን? የሚል ነው። የኦሮሞ ህዝብ ገዥ አስተሳሰብ ምንድነው? ብዬ ራሴን ስጠይቅ መልሱ ከእነርሱ በላይ ኢትዮጵያዊነት ስለማይሰማኝ ስጋት አይገባኝም። አንድ እውነታ ግን – በአንድ ወቅት ከስራዬ ጋር በተያያዘ መረጃ ለመሰብሰብ አርሲ ገጠር ድረስ ሄጄ እንዳረጋገጥኩት ኦሮሚያ ውስጥ በሃይማኖት የሚነሳ ግጭት ሰበቡ ትንሽ ስለማይሆን (በወቅቱ ክርስቲያን/ሙስልም እየተባለ በሶስት ቀን ብቻ ከ230 በላይ ቤቶች ተቃጥለው፣ ሰዎችም ተገድለው ነበር) የኦሮሚያ ህዝብ ከመቼውም በበለጠ መጠንቀቅ ያለበት ይመስለኛል። ግብፆች ኦሮሞን ደጋግመው ሲለሚያነሱ አነሳሁ እንጂ ለግጭት ተጋላጭነቱ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች መኖሩን አልዘናጋሁም። የግብፆች ሌላኛውና የሰሞኑ ሙከራቸው ደግሞ ፕሬዝደንት ትራምኘ ከተለመደው ዲፒሎማሲያዊ አሰራር ባፈነገጠ እና በመደዴ አቀራረባቸው በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫናና ማስፋራሪያ በማድረግ የአባይን ጉዳይ እናስፈፅማለን የሚል ነዉ። በሁላችን ትብብር ይህም አይሳካላቸውም።

ኢትዮጵያ በጣሊያን ለሁለተኛ ጊዜ በ1927 ዓ ም ስትወር በወቅቱ ምዕራባውያን ሞሶሎኒን ካስከፋን ከሂትለር ጋር ይወግናል በሚል ስሌት (የሗላ ሗላ ከሂትለር ጋር መወገኑ ላይቀርላቸው ) ኢትዮጵያን ለብቻ ለጣሊያን አጋፍጠው እንደ እጅ መንሻ ሰጥተው እንደነበር አይረሳንም። አሁንም ግብፅን ላለማስከፋትና ለማባበል በየአመቱ አሜሪካ ለግብፅ ከምትሰጠው ዶላር በተጨማሪ የኢትዮጵያ ልዑላዊነት አንዱ መገለጫ የሆነውን የአባይ የውሃ ሓብት መብት ለግብፅ ለመለገስ ማሰቧ ሁላችንንም የስቆጣ ነገር ነው።

አሁን ጉዳዩ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። ማገዝ ባለብን ነገር ሁሉ የኢትዮጵያን መንግስት በዚህ ጉዳይ ማገዝ የዜግነት ግዴታችን ነው።

በዚሁ አጋጣሚ በአሜሪካ የግብፆችን የተደራጀን ስራ በተመጣጠነ ልክ ለመመከት እንዲቻል ቢያንስ ግድቡ እስከሚያልቅ ወይም ሁነኛ ስምምነት እስከሚደረግ ወይም አጓጉል ውሳኔ ከሗይት ሃወስ ከመውጣቱ በፊት የኢትዮጵያ መንግስት አግባቢ (ሎቢይስት) መቅጠር አለበት የሚል ብርቱ እምነት አለኝ። ባለኝ ቅርበት እስከማውቀው ድረስ አሁን ያለው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ የግብፆችን በብዙ ሎቢስቶች የተደራጀውን ሰንሰለት ለመመከት የሚችል አይመስለኝም። ይህ ጉዳይ ፈርጀ ብዙ ብርቱ ዘማቻ ይፈልጋል። ግብፆች ይውሩናል ከሚለው ይልቅ የሗይት ሀውስ አምባገነኑ መሪ ኢኮኖሚያችንን የሚጎዳ የማናለብኝነት ውሳኔ እንዳይሰጥ ከወዲሁ ነጭን ይዞ ነጭን ማናገር ይሻላል ለማለት ነው። ግብፆች ኢትዮጵያን እንወራለን ቢሉም ባይሉም አይወሩንም (የጎረቤት ሀገሮችን -ኤርትራ/ሱዳን/ሱማሊያን-እንደእጅአዙር የመጠቀምን የግብፅ ስሌት ዶ/ር አብይ አበላሽቶባቸወዋል። በዚህም እጅግ ልመሰገን ይገበዋል ። )

እስከሚገባኝ የግብፅ ታክቲክ ኢትዮጵያን በጦር ከመውረርና እንደ ጦር ባላንጣ ከመታየት ይልቅ (ግብፅ ጦርነት ቢታወጅ በአለም ህግ መሰረት በጦርነት ያለ ሃገር በሰላም ጊዜ ስምምነት የተፈራራመውን ስምምነት በጦርነት ውስጥ ሆኖ በሌላኛው ወገን እንዲፈፀምለት የመጠየቅ መብቱን ስለሚያጣ ግብፅ በእርግጠኝነት አሸናፊ ሆና ለማትወጣው ጦርነት ብላ እጇ ላይ ያለውን ድርድር ታጣለች ብዬ ማመን ያስቸግራል)፤ ይልቁን የውስጥ ድክመቶቻችንን መጠቀምን ብሎም ማስፈራራትን፤ ብድር ለግድቡ እንዳይገኝ ማድረግን፤ እርስ በእርስ እንድንዋጋ ማድረግን፤ ከጎረቤቶቻቻን ጋር ሰላም እንዳይኖረን ማድረግ፤ አሁን ደግሞ በሃገር ውስጥ ያሉት የውስጥ ቅራኔዎችንን ማባባስን ያጠቃልላል። ከሌሎች የመካከለኛ ምስራቅ የአረብ ሀገሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የዘረጉት የደህንነት መዋቅርም እኔ እስከማውቀው ቀላል አልመሰለኝም። ኢትዮጵያ ከሚፈርሱ ሀገሮች አንዱ ናት የሚለውን የክራይስስ ግሩፕ ሟርት ግብፆች በእጅጉ ማንበባቸውን መገመቱ መጥፎ አይደልም።

አሁን ዋናው ቁም ነገር አንድ ላይ ሆኖ የሃገርን ጥቅም ማስጠበቅ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ የምንከፍለው ዋጋ አይነቱም መጠኑም ጥያቄያችን ሊሆን አይችልም።(የአዘጋጁ ማስታወሻ:- አቶ ፍሬህይወት ሣሙኤል ከምርጫ 97 ቀውስ በመንግስት የተሰየመ አጣሪ ቡድን ሰብሳቢ የነበሩ ሲሆን እውነታውን ለመደበቅ ባለመስማማት አገር ጥለው መውጣታቸውና እውነታውን ለህዝብ መግለፃቸው ይታወሳል።)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top