Connect with us

ትራምፕ የአባይ ድርድር ይቀጥል አሉ፤ ግን እንዴት እንመናቸው?

ትራምፕ የአባይ ድርድር ይቀጥል አሉ፤ ግን እንዴት እንመናቸው?
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ትራምፕ የአባይ ድርድር ይቀጥል አሉ፤ ግን እንዴት እንመናቸው?

ትራምፕ የአባይ ድርድር ይቀጥል አሉ፤ ግን እንዴት እንመናቸው? | (ታምሩ ገዳ)

በአወዛጋቢው የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከዋንኛ ተደራዳሪዎቹ እኩል የአቋም እና መመሪያ አዘል መግለጫ ያወጣው የአሜሪካው የፕ/ት ትራምፕ አስተዳደር ውይይቱ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ። ኢትዮጵያ በበኩሏ ጉዳይን በጥንቃቄ እያየችው ነው።

በትላንትናው እለት ከግብጽ አቻቻው ከፕ/ት አልሲሲ ጋር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደረጉት ፕ/ት ትራምፕ እንደ ግብጹ አልሀራም ጋዜጣ ዘገባ ካይሮ የህዳሴው ግድብ ረቂቅ ስነድን ብቻዋን አርቅቃ ብቻዋን በመፈረሟ ፕ/ት “አድንቀው”ሶስቱ ተደራዳሪዎች (ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን)ወደ ድርድር ጠረጴዛው እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዋይት ሀውስ የወጣው መገለጫን ተመርኩዞ የአሜሪካ ራዲዮ እንደ ዘገበው “ትራምፕ ድርድሩ በፍጥነት ተካሂዶ ሁለን አቀፍ ስምምነት ይደረሳል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል” ። በአሜሪካ አስተዳደር “ቅሬታ አለኝ፣ ተጽእኖ እና ጫና እየተደ ረገብኝ ነው” የሚል ቅሬታ ያሰማችው ኢትዮጵያን ማግባባት እና ልዩነቶችን ማጥበብ የተለመደ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ሆኖ ሳለ ፕ/ት ትራምፕ ግን ወደ አዲስ አበባ ሳይሆን ወደ ካይሮ ስልክ የመደወላቸው ጉዳይ ሁኔታውን ከማወሳሰብ አልፎ የትራምፕ አስተዳደር ከመጋረጃው ጀርባ ምን አስቦ ይሆን? የሚል ስጋት በበርካታ ታዛቢዎች ዘንድ መፍጠሩ አልቀረም።

በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ከታዛቢነት ወደ አደራዳሪነት መንፈስ የተሸጋገረው የአሜሪካ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ”ኢትዮጵያ በራሷ ፍቃድ በህዳሴው ግድብ የውሃ ማቆር ሆነ የመጀመሪያ ሙከራ ማድረግ አትችልም” ማለቱ ብዙዎችን አስደንግጧል፣ አስገርሟል።

በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቭድ ሹም ሁኔታውን አስመልክተው በወዳጆች መረብ በሰጡት አስተያየት”የአሜሪካ ገንዘብ ሚ/ር ያወጣው መግለጫ ለግብጽ ይሁንታ የሰጠ ይመስላል፣ ድርድሩ መስመር ሳይዝ ብችኮላ ወደ ፊርማ ግቡ መባሉ ምን ተፈልጎ እንደሆነ ያጠራጥራል”ብለውታል።

የአሜሪካ አስተዳደር የግምጃ ቤት ሹም የሆኑት ስቲቭን ሙቺን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተኑ የፊርማ ሥነሥርዓት ላይ ባለመገኘቷ አስተዳደራቸው ቅር መሰኘቱን እና የኢትዮጵያን አቋም የደገፉ ሚስተር ስቲቭን አጥብቀው የጠየቁ የምክር ቤት አባላት መበራከታቸውን ህብር ራዲዮ በምስል የተደገፈ መረጃ በትላንትናው እለት አሰራጭቷል።

ችግሮች በድርድር እና በውይይት እንደሚፈቱ ጽኑ እቋም ያላቸው የኢትዮጵያው የውጭ ጉ/ሚ/ር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው ለመገናኛ ብዙሃናት በሰጡት አስተያየት” የአሜሪካ አስተዳደር ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ውጪ ፊርማ ለማፈራረም እና ጫና ለመፍጠር ባይጣደፍ ይመረጣል”ሲሉ ማስጠንቀቂያ አዘል ቅሬታ አሰምተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በአሜሪካ መንግሥት ስሞነኛ ጣልቃ ገብነት የተቆጡ በርካታ ኢትዮጵያኖች የግብጽን እና የዋሽንግተን ገዢዎችን አቋም ለመቃወም ሲሉ “ግድቡ የእኔ፣ የእኛ ነው/It’s my dam” የሚል ዘመቻ ባመክፈት የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top