Connect with us

አምባሳደር ዴቪድ ሺን የአሜሪካ መንግሥት ለግብጽ እያደላ ነው አሉ

አምባሳደር ዴቪድ ሺን የአሜሪካ መንግሥት ለግብጽ እያደላ ነው አሉ
Photo: CGTN America

ማህበራዊ

አምባሳደር ዴቪድ ሺን የአሜሪካ መንግሥት ለግብጽ እያደላ ነው አሉ

በኢትዮጵያና በቡርኪና ፋሶ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሺን የሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ድርድርን አስመልክቶ የአሜሪካ መንግሥት ለግብጽ እያደላ ያለ ይመስላል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ከሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን እያካሄዱ ባሉት ድርድር ዙርያ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በዶናልድ ትራምፕ ተወክሎ በታዛቢነት መግባቱን እንደሚያውቁ ጠቅሰው፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ እስከ መስጠት መድረሱ ግራ እንዳጋባቸው በብሎጋቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

የትሬዥሪ መምሪያው ኃላፊ ስቲፈን ምኑቺን ባለፈው አርብ ይፋ ባደረጉት መግለጫ በአሜሪካ አደራዳሪነት ተደረሰበት ያሉትን ስምምነት ግብጽ ለመፈረም ዝግጁ መሆኗን በአድናቆት ማውሳታቸው እንግዳ ነገር ነው ብለዋል ዴቪድ ሺን፡፡

ተደራዳሪዎቹ አካላት ስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው አንዳችም በይፋ የሚታወቅ ነገር አለመኖሩን የጠቀሱት አምባሳደር ሺን መግለጫው ድርድሩ በስምምነት ሳይቋጭ የመጨረሻ ሙከራና ግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ መካሄድ የለበትም ሲል ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ አስገራሚ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ለመቀበል ዝግጁ ስለመሆኗ ምልክት እንኳ እንዳልሰጠች፣ ሌላው ቀርቶ ሱዳንም ስምምነቱን መቀበል አለመቀበሏን እንዳላሳወቀች አምባሳደር ዴቪድ ሺን አስታውሰዋል፡፡

በእንዲህ ዓይነቱ ድርድር ላይ ሚና ሊኖረውና መግለጫ ሊሰጥም የሚገባው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሆኖ ሳለ፣ የግምጃ ቤቱ መምሪያ በኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያሳድር መግለጫ ማውጣቱ አሜሪካ ለግብጽ እያደላች ነው የሚል ጥርጣሬ እንደሚያሳድር ዴቪድ ሺን በብሎጋቸው ጽፈዋል፡፡

(ዘከርያ መሐመድ~ ሸገር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top