Connect with us

ያለመደማመጥ ሀውልት?

ያለመደማመጥ ሀውልት?
Photo: Facebook

ጥበብና ባህል

ያለመደማመጥ ሀውልት?

ያለመደማመጥ ሀውልት?
(ዮሐንስ መኮንን)

ለአርኪቴክቶች እና ለከተማ ፕላነሮች ምክረ ሃሳብ “የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ” ያለው የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ከሜክሲኮ ወደቄራ በሚወስደው መንገድ ገነት ሆቴል ያለበት ቦታ ላይ “መሶብ ማማ (tower)” ብሎ የሰየመውን የመስተዋት “መሶበወርቅ” ሊገነባ ዝግጅት መጨረሱን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

(ከዚህ ቀደም የተለያዩ የዘርፉ ባለሙያዎች ከግምት እንዲገቡ ያሳሰቧቸው ጉዳዮች በሙሉ ታልፈዋል)

የኢትዮጵያ አርኪቴክቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ የከተማ ፕላነሮች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ወዳጆች እና ሌሎች የሚመለከታችሁ የሙያ እና ሲቪክ ማኅበራት የሀገር ሀብት ሳይባክን አቋም እንድትይዙ እና አስፈጻሚውን አካል እንድትወተውቱ እንጠብቃለን።

ከኪነ ሕንጻ፣ ከከተማ ፕላን እና ከሌሎች የምህንድስና ሳይንስ እሳቤዎች ሊታዩ የሚገባቸውን የቅርጽ (form)፣ የምጣኔ (proportion)፣ ተገቢነት (context)፣ … ወዘተ ላይ የሰከነ እና አጥጋቢ የባለሙያዎች ውይይት ሳይደረግበት አዲስ አበባ ላይ ከሰማይ የወደቀ (fallen from the sky) የመሰለ “ከአፍሪካ አንደኛ” ለማለት ብቻ ሕንጻ ለማቆም በመጣደፍ የምናተርፈው የስኬታችን ተምሳሌት የሆነ ማማ ሳይሆን ያለመደማመጣችን ምስክር ሃውልት እንዳይሆን ያሳስበኛል።

ከዚህ ቀደም በግሌ የታየኝን ሙያዊ ሀሳብ እንደሚከተለው አካፍዬ ነበር።

ሰሞነኛ የዲዛይን ወሬ

“በመሶብ” ቅርፅ ዲዛይን የተደረገ ባለ 70 ወለል ህንፃ በአዲስ አበባ ለማስገንባት ማሰቡን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

“የኢትዮጵያውያንን አኗኗር ያሳያል” የተባለው ህንፃ 250 ሜትር ከፍታ ያለው ባለ 70 ወለል ህንፃ ሲሆን በዚህ ርዝመቱ ከአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናል ተብሏል::

በግሌ እንደአርኪቴክት የዲዛይኑን መነሻ ሃሳብ (concept) ወካይ (metaphor) መሶብ መሆኑን ወድጄዋለሁ:: ሀገራዊ እሴትን የሚያንጸባርቅም ይመስለኛል:: (እንደወረደ መሶቡን በቁሙ “ዱብ” አድርጎ በትልቁ ማቆም ሳይሆን በዝርዝር ዲዛይኑ በማሻገር (transform) የማድረግ ሥራ እንደሚኖር ተሥፋ በማድረግ)

ስለ ቦታው (site), አከባቢያዊ ቅኝት (Urban considerations), አከባቢያዊ እሳቤዎች (environmental considerations), እና የሙቀት እና ቅዝቃዜ ምቾቶች (thermal comforts) በዝርዝር የሚነግረን ብናገኝ ደግሞ ድንቅ ነበር:: ስለዲዛይኑ ዝርዝር መረጃ ያላችሁ እስኪ ወዲህ በሉ::

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top