Connect with us

የኬንያ የግብርና ሚንስቴር የአህያ እርድ መታገዱን አወጁ

የኬንያ የግብርና ሚንስቴር የአህያ እርድ መታገዱን አወጁ።
Photo:the brooke

ህግና ስርዓት

የኬንያ የግብርና ሚንስቴር የአህያ እርድ መታገዱን አወጁ

ኬንያ የአህያ ስጋና ቆዳ በቻይና ያለውን ተፈላጊነት ታሳቢ በማድረግ ነበር የአህያን እርድን እንደ አውሮፓውያኑ 2012 ላይ ሕጋዊ ያደረገችው።

የግብርና ሚኒስትሩ ፒተር ሙኒያ የአህያ እርድን የሚፈቅደው ሕግ ስህተት እንደነበርና በአገሪቱ የአህያ ቁጥር እንዲቀነስ ማድረጉን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በገጠራማ የኬንያ አካባቢዎች ሰዎች አህያዎችን ውሃ ለመቅዳት፤ እንዲሁም እንጨት ለመጫን ስለሚጠቀሙ የአህያዎች ቁጥር መቀነስ በሴቶች ላይ ጫና እንዳያሳድር በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ተናግረዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት መንግሥት ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአሥር ዓመታት በፊት በኬንያ 1.8 ሚሊዮን አህዮች የነበሩ ሲሆን ባለፈው ዓመት ግን ቁጥራቸው 600,000 መድረሱን አስታውቋል።

ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በግብርና የሚተዳደሩ ሴቶችና ወንዶች መንግሥት አህዮችን ለመጠበቅ አንድ ነገር ያድርግ ሲሉ በናይሮቢ ከግብርና ሚኒስትሩ ሙኒያ ቢሮ ደጃፍ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ አንግበዋቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል “አህዮች ሲሰረቁና ሲገደሉ ሴቶች አህያ እየሆኑ ነው” የሚል ይገኝበት ነበር።

ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ አህያ ለማረድ ፍቃድ የተሰጣቸው ቄራዎች አህያ ማረዳቸውን አቁመው ሌላ እንስሳ በማረድ ላይ እንዲሰማሩ ካልሆነም እንዲዘጉ የአንድ ወር ጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው እንደነበር ተናግረዋል።

“አህዮችን ለስጋ ማረድ ጥሩ ሃሳብ አልነበረም” ያሉት ሚኒስትሩ፤ አህዮችን በማረድ የሚገኘው ጥቅም አህዮች ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ሲነጻጸር የሚስተካከል አይደለም በማለት ተናግረዋል።

የአህያ እርድ ሕጋዊ መሆን ለተደራጀ የአህያ ስርቆት እንዲሁም ለአህያ ቆዳ ጥቁር ገበያም ምክንያት ሆኗል።

ኬንያ አህያ እንዲያርዱ ፍቃድ የሰጠቻቸው ቄራዎች አራት ሲሆኑ እነዚህ ቄራዎች ቢያንስ በቀን አንድ ሺህ አህዮችን እንደሚያርዱ ይገመታል።

ምንጭ:-ቢቢሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top