Connect with us

የ63 ሰዎች ክስ ተቋረጠ

የ63 ሰዎች ክስ ተቋረጠ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የ63 ሰዎች ክስ ተቋረጠ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ 63 የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ክስ ማቋረጡን ይፋ አደረገ። የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ብ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው ክሳቸው አለመቋረጡ ተሰምቷል።

ክሱ የተቋረጠው ለሀገራዊ አንድነት እና ለለውጡ የሚኖረው ፋይዳን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለህዝብ እና ለሀገር ጥቅም ሲባል ነው።

ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረጉ ግለሰቦች መካከልም የሜቴክ ሰዎች እና ከሰኔ 15 የመስቀል አደባባይ የቦምብ ፍንዳታ እና በሲዳማ ዞን ተከስቶ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ግለሰቦች ይገኙበታል።


ዐቃቤ ሕግ የ 60 የወንጀል ተጠርጣሪዎች ክስ አቋረጠ

መንግስት በተለያየ ምክንያት ጉዳያቸውን በህግ ሲከታተሉ ለነበሩ 60 ዜጎች ምህረት አደረገ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ መንግስት የ60 ዜጎች ክስ ተቋርጦ ምህረት እንዲደረግ ወስኗል።

አያይዘውም የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና መንግስትም ሆነ ታራሚዎች በጉዳዩ ላይ ትምህርት የወሰዱበት በመሆኑ ምህረት መደረጉን አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈም መንግስት የዜጎችን ጥያቄ በማድመጥና ማህበራዊውን ሁኔታ በማየት መወሰኑን ተናግረዋል።

መንግስት ባደረገው ምህረት ዝርዝር ሁኔታ እና አፈጻጸም ላይም ጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።(ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top