Connect with us

የአኮኖሚ ምሁሩ ንዋይ ገብረአብ አረፉ

የአኮኖሚ ምሁሩ ንዋይ ገብረአብ አረፉ
Photo: Facebook

ዜና

የአኮኖሚ ምሁሩ ንዋይ ገብረአብ አረፉ

የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ከ20 ዓመታት ላለነሰ ጊዜ በኢኮኖሚ አማካሪነት ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ ነዋይ ያረፉት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ንዋይ ከ 20 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዝግጅት አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡

አቶ ንዋይ ገብረአብን ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ቦታ በእጩነት አቅርቦአቸው የነበረ ቢሆንም አልተሳካላቸውም፡፡

የካይዘን ፍልስፍና በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ላደረጉት አስተዋፅኦ የጃፓን መንግስት ከጃፓን መንግሥት የክብር ኒሻን ሽልማት አግኝተዋል፡፡

በጃፓን መንግሥት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1875 የተቋቋመው ”የክብር የንጋት ፀሃይ ሽልማት” ወደ ብርና ወርቅ እያደገ የመጣና ጃፓን ከሌሎች አገሮች ጋር ባላት የሁለትዮሽ ግንኙነት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የውጭ ዜጎች የሚሰጥ ሽልማት ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top