Connect with us

ሄይኒከን ፕሪሚየር ድራፍት ገበያውን ተቀላቀለ

ሄይኒከን ፕሪሚየር ድራፍት ገበያውን ተቀላቀለ

ዜና

ሄይኒከን ፕሪሚየር ድራፍት ገበያውን ተቀላቀለ

ሄይኒከን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ፕሪሚየር ድራፍት ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ፡፡ “ዴቪድ” የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ፕሪሚየር ድራፍት ልክ በቢራ ደረጃ እንደሚሸጡት በደሌ ስፔሻል እና ሄይኒከን ቢራ ለየት ያለ ጣዕምና ጥራት ያለው መሆኑን፣ ለኢትዮጵያ ገበያም እንዲህ ዓይነት ድራፍት ሲቀርብ የመጀመሪያው መሆኑን አቶ ፍቃዱ በሻህ የሃይኒከን ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ሰስተነብሊቲ ሥራ አስኪያጅ ለድሬቲዩብ ገለጹ፡፡

ዴቪድ ድራፍት ባለፈው ዓርብ ዕለት ማምሻውን ጋዜጠኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በማሪዮት ኢንተርናሽናል ሆቴል ይፋዊ የማስተዋወቅ ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡

በዕለቱ የዲቪድ ድራፍት ማሽን አነስ ያለና በቀላሉ ሊንቀሳቀስ የሚችል መሆኑን ለማየት የቻልን ሲሆን የድራፍት በርሜሉም እያንዳንዱ 20 ሊትር የመያዝ አቅም ያለውና በርሜሉን ከማሽኑ ጋር የሚያገናኘው ቱቦ ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ከዋለ በሀላ ከበርሜሉ ጋር ለፋብሪካው ተመላሽ በማድረግ እንደገና አዲስና ንጹህ በርሜል ከእነማስተላለፊያ ገመዱ (ቱቦው) ለአከፋፋዮች የሚሰጥ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ መሆኑ የድራፍት ቢራ በንጽህና ለማሰራጨት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

ዴቪድ ፕሪሚየም ድራፍት በአሁን ሰዓት ወደገበያ መግባቱም ታውቋል፡፡

ሄይኒከን ኢትዮጵያ ዋልያ፣ በደሌ፣ ሐረር፣ ሃይኒከን የተሰኙ መደበኛ እና ፕሪሚየር ቢራዎች አምርቶ የሚያከፋፍል ሲሆን በተጨማሪም ሶፊ ማልት፣ ሶፊ ቡና እና በክለር በተሰኙ ምርቶቹ ይታወቃል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top