Connect with us

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታዎች

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታዎች
Photo: exercise.co.uk

ጤና

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጠቀሜታዎች

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ከአካል ብቃት መጎልበት ባለፈ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጡንቻዎች በአግባቡ እንዲሰሩ ከማድረግ ጀምሮ የተከማቸ ስብና ካሎሪን በማቃጠል ሰውነት አስፈላጊውን ቁመና እንዲይዝ ያግዛል።

ሩጫ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ዋና፣ ክብደት ማንሳትን ጨምሮ በርካታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከታች የተጠቀሱትን የጤና ጠቀሜታዎች ያስገኛል።

1.ደስተኛ ለመሆን

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ሰውነት የጭንቀት እና ድብርት ስሜትን ለማስወገድ የሚረዳውን ሆርሞን እንዲያመነጭ ይረዳዋል።

ከዚህ ባለፈም የደስተኝነት ስሜት እና ቀና አስተሳሰብ እንዲኖር የሚያግዘውን ሆርሞን እንዲያመነጭ በማድረግ የደስተኝነት ስሜትን ያላብሳል።

2.የሰውነት የክብደት መጠንን ለመቀነስ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፈጣን የምግብ መፈጨት ሂደት እንዲኖር በማድረግና በቀን ውስጥ ብዙ ካሎሪዎችን በማቃጠል ጡንቻን በማጠንከር ክብደት እንዲቀንሱ ይረዳወታል።

3.ለጡንቻ እና ለአጥንት ጥንካሬ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጡንቻዎችን በማፈርጠም ጠንካራ አጥንት እንዲኖር ያስችላል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሰሩ ቁጥር ጡንቻዎን ማፈርጠም ከመቻልዎም በላይ ጠንካራ አጥንት እንዲኖርዎት ያግዛል።

4. ተጨማሪ ሃይል ለማግኘት

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሰውነት አቅምን ለማሳደግ ይረዳል።

ባለሙያዎችም ለስድስት ሳምንት የሚሰራ ተከታታይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰዎች በከፍተኛ ድካም እንዳይጠቁ እንደሚያደርግ አረጋግጠናል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ለከፍተኛ ድካም የሚጋለጡና እንደ ካንሰር፣ ኤች አይ ቪ / ኤድስ እና በሰውነት የእድገት በሽታዎች የተጠቁ ሰዎችን ሃይል ለመጨመር ያግዛልም ነው ያሉት።

5. በበሽታ የመጠቃት እድልን ለመቀነስ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እጥረት በበሽታ የመያዝ እድልን እንደሚጨምር ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ለዚህ ደግሞ እንቅስቃሴ አለማድረግ በደም ውስጥ ያለውን የስብ ክምችት መጠን በማሳደግ የደም ግፊት ተጋላጭነትን ከፍ እንደሚያደርግ ይገልጻሉ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ደግሞ ይህን አጋጣሚ በመቅረፍ ስር ለሰደደ የጤና ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀርፋል ነው የሚሉት።

6. ለቆዳ ጤንነት

እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖር በማድረግ የቆዳ ቀዳዳዎች ላይ የሚለጠፉ ያረጁ ሴሎችን ለማስወገድ ይረዳል።

ይህ መሆኑ ደግሞ የቆዳ ላይ ደህንነትን ለመጠበቅ በእጅጉ ይረዳል ነው የሚሉት የህክምና ባለሙያዎቹ።

7. ለአዕምሮ ጤና እና የማስታወስ ችሎታ

አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወደ አንጎል የሚሄደውን የደም ፍሰት የተስተካከለ በማድረግ ለአዕምሮ ጤና ደህንነት ይረዳል።

ከዚህ ባለፈም ለአዕምሮ እድገት የሚረዱ ሆርሞኖችን በማመንጨት ለጤናማ የአዕምሮ እድገትና የማስታወስ ችሎታን ለማሳደግ ይረዳልም ነው የተባለው።

8. ዘና ላለ ስሜት እና ለተስተካከለ እንቅልፍ

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት የሚከሰት ጫና እና የሰውነት ሙቀት በመኝታ ሰዓት ከፍተኛ ድካም ስለሚፈጥር የተስተካከለ እንቅልፍ እንዲተኙ ያግዛል።

9. ህመምን ለመቀነስ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሥር የሰደደ ሕመም እንዳይሰማ ማድረግም ሌላው ጠቀሜታው ነው።

በተለይም በሰውነት የመገጣጠሚያ ክፍሎች ላይ ህመም እንዳይሰማና የሚከሰት የህመም ስሜትን ለመቋቋም ይረዳልም ነው ያሉት።

10. በራስ መተማመንን ላማሳደግ

በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በህይወት ውስጥ የሚገጥሙ ፈተናዎችን በብቃት ለመወጣት የሚረዳውን በራስ የመተማመን ስሜት ለማዳበር እንደሚረዳ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ።

ይህም ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት አዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲዳብር የሚረዱ አዳዲስ ሴሎችን ከማመንጨቱ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ምንጭ፦ healthline.com/

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top