Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቡዳቢ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቡዳቢ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ
Photo: Facebook

ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቡዳቢ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ

ቤተክርስትያኗ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የግንባታ ቦታ ተፈቀደላት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ለቤተክርስትያን መስሪያ የሚውል የግንባታ ቦታ ጥያቄዋ መልስ ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ትናንት ምሽት በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ጋር በአቡዳቢ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለፃ ቤተክርስትያኗ ለብዙ አመታት ስታቀርበው የነበረው ይህ ጥያቄ አሁን ላይ ምላሽ አግኝቷል።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስት እና በሀገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰሩት ሰፊ ስራ ውጤቱ መምጣቱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱን አካላት አመስግነዋል፤ በሌሎች እምነቶች የሚነሱ መሠል ጥያቄዎችም በጊዜያቸው መልስ እንደሚያገኙ ጨምረው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይህንን ጥያቄ ለሶስት አስርት አመታት ያህል ስታቀርብ መቆየቷን መረጃዎች ያመለክታሉ።  (ኢ.ፕ.ድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top