Connect with us

ውሀ ፤ የማይቀረው የአፍሪካ ሀይል ምንጭ ቀን

ውሀ ፤ የማይቀረው የአፍሪካ ሀይል ምንጭ ቀን
Photo: nytimes

ፓለቲካ

ውሀ ፤ የማይቀረው የአፍሪካ ሀይል ምንጭ ቀን

ውሀ ፤ የማይቀረው የአፍሪካ ሀይል ምንጭ ቀን (አሥራት በጋሻው)

በቀጣዩ ሐሙስ የናይል ተደራዳሪዎች ዳግመኛ ዋሽንግተን ላይ ይገናኛሉ ። ድርድሩ የግድቡን ውሀ አሞላል በተመለከተ በቀረበ ረቂቅ ሰነድ ላይ ይሆናል።

ሀገራችንን ወክለው ክብ ጠረጴዛ ላይ የሚቀርቡት ባለሙያዎች እንደ እነ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ ላይ ከሆነ ጥርጣሬ የለኝም። ጉዳዩ ፖለቲካ ሆነ እንጂ።

ትራምፕ ቀደም ብለው የኛን ህልም ” ኢትዮጵያ ይህን ያህል ግድብ ምን ያደርግላታል ?”በማለት እንዳጣጣሉት የድርድሩ ወጪን በመሸፈን ሁለቱንም ተደራዳሪዎች አትላንቲክን አቋርጠው የጨዋታ ሜዳ ቀይረው አጠገባቸው ተቀመጥው ሲያነጋግሩ ጉዳዩን ቀላል አድርገው እሳቸውንና በታዛቢነት የተቀመጡትን የአለም ባንክና የዏይት ሀውስ አመራሮች በታዛቢነት ሰበብ በቅርብ ርቀት እየተመለከቱ እንዲወያዩ አልፈውም ከተስማሙ የድል ባለቤት ለመሆን ቋምጠው ነው ።

የአባይ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ከውሀ ግድብ ባለፈ ህልውናችን መሆኑን አልተረዱትም።

የሩቁን ትተን በቅርቡ በ1970 ዓ.ም መንግሥቱ ሀይለማርያም በአባይ ወንዝ ላይ አነስተኛ ግድብ ለመገንባት ማሰባቸውን ግብፅ ስትሰማ በወቅቱ የነበሩት የግብጹ መሪ አንዋር ሳዳት ”አይናችን እያየ በውሃ ጥም አናልቅም። እዛው ሄደን እንሞታለን ” ብለው አስፈራርተው ነበር።

በፈረንጆቹ 1959 በእንግሊዝ አርቃቂነት በግብፅና በሱዳን መካከል የተፈረመውን ውል ኢትዮጵያ እንደማትቀበል ሆዳቸው ቢያውቅም ዛሬም ያላዝኑበታል።

በውሃ አሞላል የጊዜ ገደብ ኢትዮጵያ ከ 4 እስከ 7 ዓመት ይወስዳል በማለት ሀሳብ ስታቀርብ ግብጽ በበኩሏ ከ12 ዓመት በፊት ምን ሲደረግ የሚል አቋም ይዛለች።

ከአለም አቀፍ አደራዳሪዎች በተጨማሪ የሀገሯን የውሀ ጥም ለማስረዳት እና ሌላውም እንዲረዳላት መጠነ ሰፊ የህዝብ ግንኙነት ስራ ጀምራለች። አለም አቀፍ ሚዲያ በመጋበዝ በገጠር እየተዘዋወሩ ደረቅ መሬት በማሳየት ገበሬዎች በማነጋገር የናይልን ወንዝ ጥቅም ያስረዳሉ። የኛ ሰዎች ለዚህ አቅም አጥተው ይሁን ፍላጎት ምንም አላየንም።

ባለፋት ወራት የግብፅ መንግሥት ባለሥልጣናት

ገበሬዎች በብዛት ውሃ የሚፈልጉ ሩዝና ሙዝ እንዳያለሙ አስጠንቅቀዋል ።በየሳምንቱ አርብ አርብ በየጸሎት ስፍራዎች ላይ ምሁራኑ ስለ ውሀ ጥበቃ ያስተምራሉ። በአለም ፍጻሜ ቀን የውሀ አባካኞች ምህረት አያገኙም በማለት ያስጠነቅቃሉ ።

አልሲሲ በጭንቀት ላይ ናቸው ። ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ተሰሚ መሆኗ ሁኔታውን አባብሶታል ። የተባባሩት አረብ ኤምሬት፣ ቻይና እና አሜሪካ በአፍሪካ ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን የሚያበቃቸውን መደላድል ከኢትዮጵያ አግኝተዋል። ”ታላቁ ግጥሚያ ”ንም ጀምረዋል።

የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ የግብፅ የህዝብ ቁጥር በየዓመቱ 1 ማሊዮን ሲጨምር ዛሬ ላይ 100ሚሊዮን ደርሷል። በዚህ አያያዝ ከቀጠለ በ2025 የውሀ እጥረት ይገጥማል ሲልም ተንብዮአል ።የትንበያ ረቂቅ በእጃቸዉ ሳይገባ እንዳልቀረ የሚጠረጠሩት ግብጻውያን ጊዜውን ቀረብ በማድረግ መረጃዎችን እንዳዛቡ ይታመናል። ግብጽ አለም አቀፍ ተሰሚነት ለማግኘት ትሮጣለች።

ሆኖም ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ ማእቀቡን በመጣስ ለደቡብ ሱዳን የጦር መሳሪያ ስታቀርብ እንደነበር አለም አቀፉ ድርጅት መስክሮባታል። የኢትዮጵያ መንግስትም በተለያየ ጊዜ መንግስት ግልበጣ ሙከራም ሆነ ተቋዋሚዎችን በመደገፍ እና ጣልቃ ገብነት ይከሳታል።

ትራምፕ ”አምባገነኑ ወዳጄ”የሚሏቸው አልሲሲ የፖለቲካ እድሜ ማራዘሚያ አጀንዳቸው የህዳሴው ግድብ እንደሆነ ባለፈው ምርጫ አሳይተዋል ።

የሀገሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድም ከአጨቃጫቂው ምርጫ አንድ ወር አስቀድመው በጉባ ተገኝተው የውሀ ሙሌት ያስጀምራሉ ብዬ እጠብቃለሁ ።

አንደኛው ኢትዮጵያዊ ተደራዳሪ እንዳሉት  ”የውሀ ቅኝ ገዥነት ፍላጎት ያናወዛት ”ግብጽ በፈንጆቹ 1870 የደረሰባትን ሽንፈት እያሰበች ከኢትዬጵያ የቀረበላትን ሁሉ መቀበል አለባት ባይባልም የኢትዮጵያንም የመልማት ህልም ልታጨናግፍ አይገባም።

በመጨረሻም ቀኑ ደርሶ  ዶ/ር አብይ በቲውተር ገጻቸው እንዳሉትም ”የአፍሪካ የሀይል ማመንጨት የድል ቀን” አብረን እናከብራለን ::

ቸር ያሰማን

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top