Connect with us

ከወጪ ንግድ በግማሽ ዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

ከወጪ ንግድ በግማሽ ዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

ኢኮኖሚ

ከወጪ ንግድ በግማሽ ዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

– 1.41ቶን ወርቅ በመላክ 66.83 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 0.37 ቶን ተልኮ 13.53 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተገኝቷል፣

በ2012 በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት ከወጪ ንግድ 1.33 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

አፈፃጸሙ ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው ገቢ ጋር ሲነፃጸር 10 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከወጪ ንግድ 1.66 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኛት ታቅዶ 1.33 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም አፈፃጸም ከአምናው ተማሳሳይ በጀት አመት ወራት ጋር ሲነጻጸር 121.27 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ተናግረዋል፡፡ አቶ ወንድሙ እንደ ገለጹት ቡና፣ አበባና ጫት ከፍተኛውን ገቢ ያስገኙ ምርቶች ሲሆኑ ወርቅ፣ ቁም እንሰሳት፣ ማር እና ብረታብረት ደግሞ ዝቅተኛ የውጪ ምንዛሪ ያስገኙ ምርቶች ናቸው፡፡

በበጀትዓመቱ 6ወራት 130,007 ቶን ቡና በመላክ 460.65 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 132,968.55 ቶን ተልኮ 364.79 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር፣ 31,628 ቶን ጫት በመላክ 164.46ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 30,453.43 ቶን ተልኮ 173.75 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከአበባ ምርት 123.13 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 225.26 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

በተመሳሳይ 1.41ቶን ወርቅ በመላክ 66.83 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 0.37 ቶን ተልኮ 13.53 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን 274,200 ቁም እንስሳት በመላክ 71.79 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 313,474 ቁም እንስሳት ተልዕኮ 32.65 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

በተጨማሪም የቅባት እህሎች 108.04 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር፣የትራጥሬ ሰብሎች 94.94 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት 99.86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ያስገኙ ምርቶች ሲሆኑ አፈጻጸማቸው ከእቅዳቸው አንፃር በቅደምተከተል 60.88 በመቶ፣72.51 በመቶ እና 85.98 በመቶ ነው፡፡

ከገዙበት ዋጋ በታች መሸጥ/under invoice/፣ምርት በክምችት መያዝ፣ የምርት ጥራትና አቅርቦት ውስንነት፣ ህገ-ወጥ ግብይት፣ ኮንትሮባንድ እና አልፎ አልፎ በሀገሪቷ የተስተዋሉ የጸጥታ ችግር የወጪ ንግድ እቅዱ እንዳይሳካ ያደረጉት ምክንያቶች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡ (ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top