Connect with us

በአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ፈተና ሆኗል

በአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ፈተና ሆኗል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ፈተና ሆኗል

የመሬት ወረራ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተና እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ።

የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣የሚመለከታቸው አካላት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በውይይት መድረኩ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ላይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለው የመሬት ወረራ ለከተማው አስተዳደር ፈተና እየሆነ መምጣቱ ተነስቷል።

ሙስናና ብልሹ አሰራር፣ የመረጃ አያያዝ ማነስ፣ የግልጽነትና ተጠያቂነት ችግሮች ከህግ ስርአቶች አለመከበር ጋር ተዳምረው ለመሬት ወረራው መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል ተብሏል።

ችግሩን ለመቅረፍ በቂ በሚባል ደረጃ የማስተካከያ እርምጃ ለምን መውሰድ አልተቻለም በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይም ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በአዲስ አበባ ደረጃ ችግሩን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት በሚለው ላይም እየተወያዩ ነው።(ፋና)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top