Connect with us

የቤተ ክርስቲያኒቱ ህብረት ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያን ከሰሰች

የቤተ ክርስቲያኒቱ ህብረት ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያን ከሰሰች
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የቤተ ክርስቲያኒቱ ህብረት ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያን ከሰሰች

ጣቢያው በዘገባዎቹ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም አጉድፏል ተብሏል

ጴጥሮሳውያን ህብረት የተሰኘውና ለቤተ ክርስቲያን መብት መጠበቅ እንደሚሟገት የገለፀው ማህበር፤ የኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ክስ ማቅረቡን ገለፀ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ህብረት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለሠላም ሚኒስቴር፣ ለሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ለምርጫ ቦርድ፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነትና ለሌሎች ተቋማት ግልባጭ አድርጐ ለብሮድካስት ባለስልጣን ባቀረበው አቤቱታ ኦኤምኤን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠለሹ ዘገባዎችን አስተላልፏል ብሏል፡፡

ህብረቱ ባቀረበው ክስ ላይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ በሰሜን ሸዋ ባካሄደው “የምርጫ ቅስቀሳ” ላይ የሀገሪቱን ህገ መንግስትና የምርጫ ህግ በተፃረረ ሁኔታ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለጥቃት የሚያጋልጥ ቅስቀሳና የሃሰት ውንጀላ ፈጽሟል፤ ይህንንም ኦኤምኤን በጣቢያው አስተላልፏል ብሏል፡፡

በተጨማሪም ኦኤምኤን ስለ ቤተክርስቲያኒቱ በሚያስተላልፋቸው የተዛቡ መረጃዎች የተነሳ የዘንድሮ የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለታየው ችግር መነሻ ሆኗል ብሏል – ህብረቱ፡፡

ህብረቱ በክስ ደብዳቤው፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የተላለፉ የጥላቻ መልዕክቶች ያላቸውንም በዝርዝር አቅርቧል፡፡ በቴለቪዥን ጣቢያው ከተሰራጩ መልዕክቶች መካከልም ‹‹ቤተ ክርስቲያን የፖለቲካ ኢምባሲ ናት›› ‹‹የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት››፣ የፊውዳሎች የፖለቲካ ኤምባሲ መፍረስ አለበት›› የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡

ኦኤምኤን ባሠራጨው በዚህ ፕሮግራሙ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ አለም አቀፋዊት የሆነችውን የኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ለተወሰኑ ቡድኖች የሚሰጥ ሆኗል ብሏል – ህብረቱ፡፡

በዚህም የቤተክርስቲያኑቱን በጐሣና በሃይማኖት ከፋፋይ እንደሆነች አድርጐ በማቅረብ ክብሯን የተዳፈረ ፕሮግራም ተሠራጭቷል ብሏል፡፡

የብሮድካስት ባለስልጣንም ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ህብረቱ ጠይቋል::

ምንጭ:-  አዲስ አድማስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top