Connect with us

“በግርግሩ የታሠሩ ወጣቶች ሁሉም እንዲፈቱ አድርገናል” ፡- ኢ/ር ታከለ ኡማ

“በግርግሩ የታሠሩ ወጣቶች ሁሉም እንዲፈቱ አድርገናል” ፡- ኢ/ር ታከለ ኡማ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“በግርግሩ የታሠሩ ወጣቶች ሁሉም እንዲፈቱ አድርገናል” ፡- ኢ/ር ታከለ ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ በተፈጠረ ግርግር የታሠሩ ወጣቶች ሁሉም እንዲፈቱ መደረጉን የከተማዋ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስታወቁ፡፡

የተፈጸመውን አሳዛኝ ድርጊት በቦታው ተገኝቼ ተመልክቻለሁ ያሉት ም/ከንቲባው የሟች ቤተሰቦችንም ለማጽናናት በቤታቸው ተገኝተው እንደነበር ገልፀው ሁሉም ነገር ልብ ይሠብራል ብለዋል ።

ም/ከንቲባው በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በቀጣይም በዚህ ሁኔታ ለተጎዱ አካላት የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ኢ/ር ታከለ ይህንን ወቅት በትዕግስት እና በአስተዋይነት የማረጋጋት ሥራ ለሠሩ ወጣቶች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሃይማኖት አባቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ ከቤተክርስቲያን ግንባታ ጋር በተያያዘ በነዋሪዎችና በፀጥታ ሀይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሁለት ወጣቶች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡(ኢ.ኘ.ድ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top