Connect with us

በአዲስ አበባ ተግባራዊ የተደረገው የLte advance 4G ኔትወርክ አገልግሎት ከቀድሞዎቹ በምን ይለያል?

በአዲስ አበባ ተግባራዊ የተደረገው የLte advance 4G ኔትወርክ አገልግሎት ከቀድሞዎቹ በምን ይለያል?
Photo: Facebook

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

በአዲስ አበባ ተግባራዊ የተደረገው የLte advance 4G ኔትወርክ አገልግሎት ከቀድሞዎቹ በምን ይለያል?

አዲስ አበባ ጥር 25/2012፡- ኢትዮ ቴሌኮም የLte advance 4G አገልግሎት በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ተግባራዊ ያደረገው የLte advance 4G አውታረ-መረብ(network) አብዛኛው ማህበረሰብ እየተጠቀመበት ካለው ከሁለተኛ ትውልድ (2G) ፣ ከሦስተኛው ትውልድ (3G) እና ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ከሆነው ከአራተኛው ትውልድ (4G) በምን ይለያል?

‘G’ የሚለው የእንግሊዘኛ ፊደል ቴክኖሎጂው የደረሰበት ‘ትውልድ’ /Generation/ የሚወክል መጠሪያ ነው፡፡ 3G፣4G፣ 4G LTE እና 5G VoLTE ከስማርት ስልኮች ጋር በተገኛኘ በአብዛኛው የሚነሱ ስያሜዎች ናቸው፡፡

የምንጠቀምባቸውን ስልኮች ከበይነ-መረብ(internet) ጋር ስናገናኝ የበይነ-መረቡ ፍጥነት የሚወሰነው በምንጠቀመው የማስተላለፊያ አቅም ሲሆን ይህም 1G፣ 2G፣ 3G፣4G፣ 4G LTE እንዲሁም 5ጂ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ እያንዳንዱ ትውልድ /Generation/ በስልክ አውታረ-መረብ ደረጃዎች /set of telephone Network Standards/ የተሰላ ነው፡፡
ፍጥነቱ ሲጨምርና ያንን ለማሳካት የምንጠቀምበት ቴክኖሎጂ ፍጥነትም እየተለወጠ ይመጣል፡፡

ለምሣሌ፡-
• 1G የሚሰጠን 2.4 Kbps፣
• 2G የሚሰጠን 64 kbps እና በተንቀሳቃሽ የስልክ ዓለም አቀፍ ሥርዓት /GSM/ መሠረት፣
• 3G የሚሰጠን 144 kbps – 2mbps፣
• 4G የሚሰጠን 100Mbps -1Gbps እና የረጅም ዘመን ቴክኖሎጂ ለውጥ /LTE technology/ ውጤት ነው፡፡
በአለም አቀፉ ማህበረሰብ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት የአውታረ-መረብ ደረጃዎች

#1. የሁለተኛ ትውልድ/2G/ አውታረ-መረብ
የሞባይል ስልኮች የመጀመሪያውን ማሻሻያ ያደረጉት ከመጀመሪያው ትውልድ /1G/ ወደ ሁለተኛው ትውልድ /2G/ ሲያድጉ ነው፡፡

ዋነኛ ልዩነታቸውም 1G የራዲዮ ሲግናል /Analog/ ተብሎ የሚጠራውን የሚጠቀም ሲሆን 2G ግን ዲጂታል /Digital/ የተሰኘውን ሥርዓት የሚጠቀም መሆኑ ነው፡፡

የሁለተኛ ትውልድ መተዋወቅ ዓላማም ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ የኮሙዩኒኬሽን ቻናል ለማቅረብ ነበር፡፡
#2G ዋና ዋና ገጽታዎች

 2G CDMA እና GSM የተባሉ ፅንሰ ሀሳቦችን ተግባራዊ ያደረገ ቴክኖሎጂ ነው፤
 የ2G የመጨረሻ የፍጥነት አቅም 64 Kbps እስከ 1mbps ነው፤
 መልዕክት /SMS/ እና ባለብዙ ዓይነት መልዕክት መላኪያ /MMS/ አገልግሎትን መጠቀም ያስችላል
 የተሻለ የድምጽ ጥራት ያላቸውን ጥሪዎች ያቀርባል
 ከ 30 እስከ 200 ኪሎ-ህረዝ /KHz / ባንድ ባንድዊድዝ ይጠቀማል፡፡

#_2ሦስተኛ ትውልድ (3G) አውታረ-መረብ
ሦስተኛው ትውልድ ለአብዛኞቹ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂዎች ስታንዳርድ ያስቀመጠ ነበር፡፡ ለአብነትም ዌብ ማሰስ /web browsing/፣ ኢ-ሜይል፣ ቪዲዮ ማውረድ፣ ምስሎችን መጋራት እንዲሁም ሌሎች የስማርት ስልክ ቴክኖሎጂዎች የተዋወቁት በሦስተኛው ትውልድ ነው፡፡

የ3G አውታረ-መረብ ዩኒቨርሳል የሞባይል ቴሌኮሙዩኒኬሽን ሲስተም (UMTS)ን እንደ ዋና የአውታረ-መረብ ንድፍ የሚጠቀም ነው፡፡ 3ጂ አውታረ-መረብ እጅግ በጣም ፈጣን የሆነ ዴታ መጠንን ለማቅረብ የ2G አውታረ-መረብ ገጽታዎችን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና ፕሮቶኮሎች ጋር በማጣመር ያቀረበ ነው፡፡

#የ3G-ዋና ዋና ገጽታዎች
 የ3G UMTS /Universal Mobile Telecommunications System/ የተሰኘ አውታረ መረብ ይጠቀማል
 የ3G የመጨረሻ የፍጥነት አቅም 144 kbps እስከ 2mbps ነው፤
 ግዙፍ የኢ-ሜይል መልዕክቶችን በቀላሉ ለመላክና ለመቀበል ያስችላል፡፡

 የተሻለ የድምጽ፣ የዳታ አቅም፣ ሰፊ ሽፋን ያለው ተግባር የሚደግፍ እና የመረጃ ልውውጥን በዝቅተኛ ዋጋ የሚያሳድግ ነው፡፡
 የዴታ የማስተላለፍ አቅሙ እና የባንድ ዊደዝን መጠኑ ከሁለተኛው ትውልድ የጨመረ ነው፡፡
 ብሮድባንድ የመሸከም አቅሙ ከፍ ያለ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

#አራተኛ_ትውልድ (4G) አውታረ-መረብ
በ3G እና በ4G መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት “የዴታ” መጠን ሲሆን በመካከላቸውም ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ይህም 4G ኔትዎርክ ቁልፍ ቴክኖሎጂ የሆኑትን MIMO (Multiple Input Multiple Output) እና OFDM (Orthogonal Frequency Division Multiplexing) በመያዙ ነው፡፡

እጅግ አስፈላጊ ከሆኑት 4G መስፈርቶች መካከልም ‘WiMAX’ /አሁን ላይ ከአገልግሎት ውጪ የሆነ/ እና ‘LTE’ም /በሰፊው ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ/ ይገኙበታል። የ4G LTE ከ3G ፍጥነቱ ዋነኛው መሻሻል ቢሆንም በቴክኒካዊ ጉዳይ 4G የተለየ ነው፡፡
#በ4G እና በ4G LTE መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

የ4ጂ አውታረ-መረብ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የአለም ክፍሎች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ቢሆንም እነዚህ አውታረ-መረቦች ተፈላጊውን የበይነ-መረብ ፍጥነት ማስገኘት አልቻሉም፡፡ ይህን ተከትሎም የ4G LTE በጣም ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የበይነ-መረብ ግንኙነትን ለማቅረብ የሚያስችል ሆኖ ቀርቧል፡፡ በመሰረታዊነት 4G ለተንቀሳቃሽ አውታረ-መረብ ግንኙነቶች አስቀድሞ መመዘኛ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ 4G LTE አውታረ-መረብ በአራተኛው ትውልድ ቀድመው የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟላ እና ለመተግበር ያግዝ ዘንድ ለተሰራ የአውታረ-መረብ የተሰጠ ስም ነው፡፡

የ4G LTE አንዳንድ ገጽታዎች፡-
 የ4G ተክኖሎጂ እውን እንዲሆን MIMO /Multiple Input Multiple Output OFDM /Orthogonal Frequency Division Multiplexing/ ተግባራዊ ተድርጓል፤
 ከፍተኛ ፍጥነት፣ ከፍተኛ ጥራት፣ ከፍተኛ አቅም ያለው ነው፤
 የተሻለ ደህንነት፣ የድምጽ፣ የመረጃ ማከማቻ፣ የባለብዙ ሚዲያ አገልግሎት /MMS/ እና በይነ-መረብ አገልግሎት በአነስተኛ ዋጋ የሚሰጥ ነው፤
 የተሻሻሉ መተግበሪያዎች የሞባይል ዌብን ለመጠቀም ማሻሻያ የተደረገባቸው /IP telephone/፣ የጌም አገልግሎት፣ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ቪዲዮ ኮንፍረንስ፣ 3D ቴሌቪዥን እና ክላውድ ኮምፒውቲንግ /Cloud Computing/ ለመጠቀም የሚያስችል ነው፡፡

LTE /Long Term Evolution/ የ UMTS ቴክኖሎጂ መሻሻል ውጤት የሆነ እና እስከ 1800 MHz ፍሪኮንሲ ባንድ ያለው ነው፡፡ ይህም በሚገርምና በከፍተኛ መጠን የመረጃዎችን ማውረድ አቅምን በ600 mbps እና 1.2Gbps መካከል ከፍ ያደረገ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

#የ4G LTE አድቫንስድ
የ4ኛው ትውልድ አውታረ-መረብ አገልግሎቶች በምንጠቀምበት ወቅት የእውነታው አለም የበይነ-መረብ መረጃዎችን የማውረድ ፍጥነት በሰከንድ እስከ 15 ሜጋ ባይት ሲሆን ይህም እንደምንጠቀምበት መሳሪያ ይለያል፡፡ ከዚህ ባለፍ የአውታረ-መረቡ ተጋሪዎች ቁጥር መጨመር የአውታረ-መረቡን የፍጥነት መጠን ይቀንሰዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም የ4ጂ የአውታረ-መረብ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ የሆነ ሲሆን ሰሞኑን የ4G LTE አድቫንስድ አውታረ-መረብ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ፍጥነቱ እስከ 300 ሜጋ ባይት በሰከንድ ፋይሎችን እንዲያወርድ በማሰብ ቢሆንም በእውነታው አለም ግን ፍጥነቱ እዚህ ቁጥር ላይ አይደርስም፡፡

ከዚህ ባለፈ እንደምንጠቀምበት ስልክ አልያም ሌላ መሳሪያ ፍጥነቱ ዝቅም ከፍም የሚል ሲሆን ከ42 ሜጋ ባይት እስከ 90 ሜጋ ባይት በሰከንድ መረጃዎችን ማውረድ የሚያስችል አቅም ያለው እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ አዲስ አበባ ተግባራዊ የሆነው 3. የ4G LTE አድቫንስድ ከ4ጂ LTE በሶስት እጥፍ የተሻለ ፍጥነት አለው፡፡(ኢመደኤ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top