Connect with us

ጥምቀትን መሰረት አድርጎ በጎንደር ከቱሪዝም ተገኘ የተባለው ገቢ የተጋነነ መሆኑ ተገለጸ፡

ጥምቀትን መሰረት አድርጎ በጎንደር ከቱሪዝም ተገኘ የተባለው ገቢ የተጋነነ መሆኑ ተገለጸ፡
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ጥምቀትን መሰረት አድርጎ በጎንደር ከቱሪዝም ተገኘ የተባለው ገቢ የተጋነነ መሆኑ ተገለጸ፡

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓልን መሠረት አድርጎ ወደ ከተማዋ ከገቡት እንግዶች የተገኘውን ገቢ አስመልክቶ እስከ 3.5 ቢሊዮን ብር ይደርሳል የሚለው መረጃ አነጋጋሪ ኾኗል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የስራ ሃላፊን ጠቅሶ ከበዓሉ የተገኘው ገቢ 3.5 ቢሊዮን ይደርሳል የሚል ዜና ለቋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዜናና እንደ ባህልና ቱሪዝም መረጃ ሰጪው ከሆነ ይላሉ በጎንደር የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘርፍ የተሰማሩ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው፤ “እርግጥ የተባለውን ያህል በቢሊዮን የሚቆጠር ገቢ ከተገኘ ከተማዋ ከዚሁ የንግድ እንቅስቃሴ ቢያንስ ከአምስት መቶ ሚሊዮን ያላነሰ የታክስ ገቢ ታገኝ ነበር ግን ቁጥሩ የተጋነነ ስለሆነ እውነታው እንደዚህ አይደለም ይላሉ፡፡”

ድሬቲዩብ ያነጋገራቸው የጎንደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ባልደረባ ደግሞ ቁጥሩ ገና እየተጠና መሆኑን ነው የሚናገሩት፡፡ በሌላ በኩል እንዲህ ያለው የተጋነነ ቁጥር በአንድ ኩነት አንዲት ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አገኘች በሚል መንግስት ለጎንደር ቱሪዝም ማድረግ ያለበትን ድጋፍ እንዳያደርግና አሁንም በቱሪዝም መዳረሻዋ ላይ ያለውን ችግሮች በሚመለከተው የክልልና የፌዴራል ተቋማት ድጋፍ እንዳትቀርፍ የሚደረግ ግነት የተሞላ መረጃ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ፡፡

እንዲህ ያሉ ቁጥሮች በዘፈቀደ መሰጠታቸው መንግስት ከተገኘው ገቢ ራሷን ማልማት አለባት ወደሚል ያልተገባ እይታ እንዲገባ የሚያስገድድ እንደሆነ ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ይህ ተገኘ የተባለው ገቢ መጠን የከተማዋን በጀት በብዙ እጥፍ የሚበልጥ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ጎንደርን በሚመለከት በቅርቡ የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስት በአራት መቶ ሚሊዮን ብር በጀት ሊጠገን ነው በሚል የተሰራው ዜና የተሳሳተ ሆኖ መገኘቱና ጉዳዮን በተመለከተ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት የሚያውቁት ነገር እንደሌለ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top