Connect with us

ሚዲያዎቻችን ቀስ!…ኸረ እባካችሁ ቀስ!…

ሚዲያዎቻችን ቀስ!...ኸረ እባካችሁ ቀስ!...
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ሚዲያዎቻችን ቀስ!…ኸረ እባካችሁ ቀስ!…

ሚዲያዎቻችን ቀስ!…ኸረ እባካችሁ ቀስ!…

(ጫሊ በላይነህ)

የጠ/ሚኒስትሩ የፕረስ ሴክሬቴሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ታገቱ ስለተባሉት ተማሪዎች በከፊል የመለቀቃቸውን የምስራች ከትላንት በስቲያ ነግረው ነበር፡፡ በእሳቸው ገለጻ መሠረትም በዶምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች ጫካ ውስጥ ታግተው መቆየታቸውን አረጋግጠው ለማሰለቀቅ በተደረገው ጥረት 13 ሴቶች እና 8 ወንድ ተማሪዎች በድምሩ 21 ተማሪዎች ማስለቀቅ መቻሉን ይፋ አድርገዋል፡፡ በአሁን ሰዓትም 6 ተማሪዎች ገደማ በእገታ ላይ መሆናቸውም አቶ ንጉሱ ጠቆም አድርገዋል፡፡

በአቶ ንጉሱ ጥላሁን መግለጫ ውስጥ ሁለት ትልልቅ ቁምነገሮች ተነስተዋል ብዬ አስባለኹ፡፡ አንዱና ዋናው የተማሪዎች መታገት በመንግሥት ደረጃ በይፋ መታመኑ ሲሆን ሌላኛው የታጋቾች ቁጥር ቀደም ሲል ሲነገር ከነበረው ከ 17 ወደ ወደ 28 ገደማ መጨመሩ መረጋገጡ ነው፡፡

በአሁን ሰዓት ያልተለቀቁ ተማሪዎች አሉ፡፡ መንግሥት ለጊዜው ስማቸውን ካልጠቀሳቸው አካላት ጋር ድርድሩን መቀጠሉ ተጠቁሟል፡፡ ይህ ይሳካ ዘንድ ነገሩን በጥሞና መከታተል ግድ ይላል፡፡

አቶ ንገሱ መግለጫ ከሰጡ በኋላ የአጋቾቹን ማንነት ለምን በግልጽ አልተነገረም የሚሉ እና ልጆቻችን እስካሁን ስለመለቀቃቸው አላወቅንም የሚሉ ቤተሰቦች ድምጾች በርክተዋል፡፡ በእኔ ዕይታ ምናልባት መንግሥት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት የተቆጠበበት ከጸጥታ ሥራ ጋር በተገናኘ የራሱ በቂ ምክንያት ሊኖረው እንደሚችል እገምታለኹ፡፡ አቶ ንጉሱ የገለጹት 21 ገደማ ተማሪዎች መለቀቃቸውን እንጂ ወደቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን አይደለም፡፡ ይህ ማለት ምናልባት ተማሪዎች ከአንድ ወር በላይ ታግተው እንደመቆየታቸው በቂ ዕረፍት፣ በቂ የሕክምና ምርመራና የሥነልቦና ድጋፍ ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል መገመት ጠንቋይ መሆንን አይጠይቅም፡፡ በዚህም ምክንያት መንግሥት ተማሪዎቹን በአንድ ቦታ ስለማቆየቱ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አለመቀላቀላቸው መነገሩ በራሱ ጠቋሚ ነው፡፡

ሆኖም እንደቢቢሲ፣ የአሜሪካ ድምጽ እና የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዓይነት ትላልቅ ሚዲያዎች የታጋች ቤተሰቦችን በማነጋገር “ልጆቹ አልተለቀቁም” የሚል ጫፍ አንጠልጥለው ነገሩን ለማጦዝ (ሴንሴሽናል ለማድረግ) መሞከራቸው በጋዜጠኝነት ሥነምግባር ማህበረሰባዊ ኃላፊነትን መጣስ ወይንም መጻረር ሆኖብኛል፡፡ በዚህም ምክንያት የአዘጋገብ መንገዳቸው ኃላፊነት የጎደለው ነው እላለኹ፡፡ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንማ የተማሪዎቹ መታገት ዜና በዝምታ እንዳልሰሙ ከርመው ለማስተባበል ሲሆን ከየጎሬአቸው ብቅ ማለታቸው የሚያሳዝን፣ የሚያስተዛዝብም ጭምር ነው፡፡ ከጋዜጠኝነት ሥነምግባር አንጻርም ይህ ሲበዛ ነውር ነው፡፡

አሁን ጥያቄው ተለቀቁ የተባሉት ልጆች የት ነው ያሉት ከሆነም አቶ ንጉሱ ጥላሁን ወይንም ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ኃላፊዎችን አስጨንቆ ተጨማሪ መረጃ ፤ለማግኘት መሞከር እንጂ ጫፍ ይዞ ስሜት ቀስቃሽ ዜናዎችን መሥራት ላይ ማተኮር ተገቢ ነው ብዬ አላንምንም፡፡ መደበኛ ሚዲያው፤ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር አጉል ፉክክር ውስጥ በመግባት ስሜታዊ የሆኑ ዜናዎችን ወደመልቀቅ ማጋደሉ በራሱ እጀግ አደገኛና በጥንቃቄ ታይቶ በአስቸኳይ እርምት ሊወሰድበት የሚገባው ብዬ አስባለኹ፡፡ በጥቅሉ እንዲህ ዓይነቱ ዘገባም ለአገር ሠላምና መረጋጋት አዎንታዊ ሚና ይኖረዋል ብዬም አላስብምና ቢታረም?!

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top