Connect with us

በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ቀን 8 ሺህ 493 ህፃናት በኢትዮጵያ ተወልደዋል

በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ቀን 8 ሺህ 493 ህፃናት በኢትዮጵያ ተወልደዋል-የመንግስታቱ ድርጅት
Photo: Facebook

ዜና

በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ቀን 8 ሺህ 493 ህፃናት በኢትዮጵያ ተወልደዋል

በፈረንጆቹ 2020 የመጀመሪያ ቀን 8 ሺህ 493 ህፃናት በኢትዮጵያ ተወልደዋል-የመንግስታቱ ድርጅት

በአውሮፓዊያኑ 2020 አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን በኢትዮጵያ 8 ሺህ 493 ህፃናት መወለዳቸውን የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ፈንድ/ዮኒሴፍ/ አስታወቀ፡፡

በአለማችን በ2020 አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ከ392 ሺህ በላይ ህጻናት መወለዳቸውንም ዮኒሴፍ አሳውቋል፡፡

ህንድ፣ ቻይና እና ናይጄሪያ ህፃናት ወደ ምድራችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት የተቀላቀሉባቸው ቀዳሚዎቹ ሶስት አገራት ሆነዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ፈንድ/ዮኒሴፍ/ ትንበያን መሰረት አድርጎ በሚያወጣው መረጃ በ2020 አዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ቀን ላይ ህንድ 67 ሺህ 385 ህጻናት ፤ቻይና 46 ሺህ 299 ህጻናት እና ናይጄሪያ 26 ሺህ 39 ህጻናት የሚወለዱባቸው ሀገራት መሆናቸውን መረጃ ያመለክታል፡፡

በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ቀን 8 ሺህ 493 ህፃናት መወለዳቸው ተጠቅሷል፡፡

ትንሿ የደሴት ሀገር ፊጂ በፈረንጆቹ አዲስ አመት የመጀመሪያው ህጻን የተወለደባት አገር ሆናለች፡፡

ይህንንም በማስመልከት ለወላድ እናቶችና ህጻናት የተሻለ ጤና ክብካቤና ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው ዮኒሴፍ ገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ በ2018 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት መከላከል በሚቻል ህመም በተወለዱ በመጀመሪያ ወር መሞታቸውን ተነግሯል፡፡

ከእዚህ ውስጥም 33 በመቶ የሚሆኑት ህይወታቸው የሚያልፈው በተወለዱበት ቀን መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በርካታ እናቶችና ጨቅላ ህጻናት ባልሰለጠኑ አዋላጅ ነርሶች አማካኝነት ስለሚወልዱ ውጤቱ አስከፊ እየሆነ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አልጃዚራ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top