Connect with us

በኢትዮጵያ ከፍተኛው ወርሃዊ የጡረታ አበል ተከፋይ 153 ሺ ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 1ሺ 258 ብር ነው

በኢትዮጵያ ከፍተኛው ወርሃዊ የጡረታ አበል ተከፋይ 153 ሺ ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 1ሺ 258 ብር ነው
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ ከፍተኛው ወርሃዊ የጡረታ አበል ተከፋይ 153 ሺ ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 1ሺ 258 ብር ነው

በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የምዝገባና አበል መወሰኛ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ እምሩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት ለጡረተኞች የሚከፈለው አጠቃላይ ዓመታዊ ክፍያ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ዝቅተኛ ወርሀዊ ክፍያ 1ሺ 258 ብር ሲሆን ትልቁ ደግሞ 153 ሺ ይደርሳል ፡፡

ከፍተኛ የጡረታ አበል የሚከፈላቸው ዜጎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ ከከፍተኛ ተከፋዮች መካከል ካፕቴኖች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ ሰባት መቶ ሀምሳ ሺ የሚደርሱ ጡረተኞች እንደሚገኙና ኤጀንሲው በዓመት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የጡረታ አበል እንደሚከፈል የገለጹት ዳይሬክተሩ በአንጻሩ ደግሞ በአመት አስራ ሁለት ቢሊዮን ብር እየተሰበሰበ ነው፡፡

ኤጀንሲው በአራት ዓመት አንድ ጊዜ የጡረታ ማስተካከያ የሚያደርግ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ፤ሆኖም ነባራዊ ሁኔታዎችን በመመልከት እንዳስፈላጊነቱ ማስተካከያ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዘጠኝ አይነት የማህበራዊ ዋስትና አይነቶች ቢኖሩም በኢትዮጵያ እየተተገበሩ ያሉት ግን አራቱ ብቻ ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ አንደኛ በእድሜ፣ ሁለተኛ በጤና ምክንያት እና ሦስተኛ በስራ ላይ እያሉ በገጠመ ችግር በደራጎት የሚወጡና ባለመብቱ ሲሞት ለተተኪዎች የሚሰጥ፤ እናትና አባት ልጆች እንዲሁም የትዳር አጋርን የሚያካትት መሆናቸውንም አስረድተዋል። (ኢፕድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top