Connect with us

ፃም ለጤናማ ሕይወት እና ረጅም ዕድሜ ለመኖር ሊያግዝ ይችላል

ፃም ለጤናማ ሕይወት እና ረጅም ዕድሜ ለመኖር ሊያግዝ ይችላል
Photo: Blue Zone

ጤና

ፃም ለጤናማ ሕይወት እና ረጅም ዕድሜ ለመኖር ሊያግዝ ይችላል

በቀን በስድስት ሰዓታት ልዩነት ውስጥ መመገብ ወይም ለ18 ሰዓታት አለመመገብ ለጤናማ ሕይወት እና ረጅም ዕድሜ ለመኖር ሊያግዝ እንደሚችል የኒው ኢንግላንድ የሥነ-መድኃኒት ጆርናል ጥናት ጠቆመ።

ምንም እንኳን ረሃብን ለመቋቋም ልምምድ ማድረግ ቢጠይቅም በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓታት ምግብ ሳይበሉ መቆየት የተለያዩ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ቁልፍ ሊሆን እንደሚችል ነው የተጠቆመው።

ጥናቱ እንደሚለው ከሆነ ባለፉት ጊዜያት በእንስሳት እና በሰዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አልፎ አልፎ አለመመገብ የደም ግፊትን እና የክብደት መጠንን ለመቀነስ እንዲሁም ረጅም ዕድሜ ለመኖር ይረዳል።

የጤና ባለሙያዎች ከመጠን በላይ ውፍረትን፣ ካንሰርን፣ ስኳር በሽታን እና የልብ ሕመምን ለመከላከል አለመመገብን እንደ አንድ መፍትሔ ሀሳብ ለማቅረብ ይህ ጥናት እንደ አንድ ፍኖተ ካርታ ሊጠቅም እንደሚችልም ተነግሯል።

ጥናቱን ያደረጉት እና በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የነርቭ ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ማርክ ማትሰን ሁለት ዓይነት የፆም መንገዶች መኖራቸውን ይናገራሉ።

የመጀመሪያው፣ በሰዓታት የተገደበ ዕለታዊ አመጋገብ (ማለትም ከ6 እስከ 8 ሰዓታት ልዩነት ውስጥ መመገብ ወይም በቀን ከ16 እስከ 18 ሰዓታት መፆም) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አልፎ አልፎ መፆም (ማለትም በሳምንት ሁለት ቀን መፆም ናቸው)።

ጥናቱ በዓይነቱ አዲስ በመሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች ሕሙማንን በሂደት አልፎ አልፎ እንዲፆሙ በማድረግ ክትትል እንዲያደርጉ እና የፆሙን ጊዜ እና ድግግሞሽ እያሳደጉ በመሄድ ለውጣቸውን እንዲመረምሩ የጥናቱ ሪፖርት ይመክራል ሲል ሲኤንኤንን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top