Connect with us

ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለሀብት ብክነትና ለዜጎች የኑሮ መጎሳቆል መንስኤ ሆኗል

ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለሀብት ብክነትና ለዜጎች የኑሮ መጎሳቆል መንስኤ ሆኗል
Photo: Sugar corporation

ኢኮኖሚ

ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለሀብት ብክነትና ለዜጎች የኑሮ መጎሳቆል መንስኤ ሆኗል

ጣና በለስ የተቀናጀ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በርካታ ስራዎችን የያዘ ነው፡፡ ከበለስ ወንዝ የመስኖ ውሃ መጥለፍ፤ በ75,000 ሄክታር መሬት ላይ ሸንኮራ አገዳ ማልማት፤ አርሶ አደሮችን ከመሬታቸው ላይ በማንሳት በሰፈራ ማዕከላት ማስፈር፤ መሰረተ ልማት ማሟላት እና ሶስት የስኳር ፋብሪካዎችን መገንባት ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ ስራዎች ለ69,000 ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ እና በዓመት 7,620,000 ኩንታል ስኳር ፣ 62,481 ሜ ኩብ ኢታኖል እና 135 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል ማምረት እንደሚያስችሉ ግብ ተቀምጧል፡፡ ስራዎቹ በ2003 ዓ.ም ተጀምረው በአራት ዓመታት እንዲያልቁም ጊዜ ተቆርጦላቸው ነበር፡፡

የዚህን ፕሮጀክት አፈፃፀም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ጎበኝተዋል፡፡ ከሶስቱ የስኳር ፋብሪካ ግንባታዎች የበለስ ቁጥር – 1 በጥሩ ደረጃ ላይ ከመገኘት በቀር የበለስ ቁጥር – 2 እና የበለስ ቁጥር – 3 ግንባታ ተቋርጦ ነው የቆየው፡፡

የበለስ ቁጥር – 2 ግንባታ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 25 በመቶ አከናውኖ ለስኳር ኮርፖሬሽን አስረክቦ የወጣ ሲሆን የግንባታ ቦታው በጫካ ተውጦ የፋብሪካ ዕቃዎች በአፈር እየተበሉ ብልሽት ላይ መሆናቸውን ነው አባላቱ ተዘዋውረው የተመለከቱት፡፡ ሌሎች የፋብሪካው ዕቃዎችም ሜዳ ላይ ያለመጠለያ ተቀምጠው ፀሐይና ዝናብ ሲፈራረቅባቸው እንደቆዩ የኮሚቴው አባላት ለመገንዘብ ችለዋል፡፡

በለስ ቁጥር – 3 ግንባታ 18 ሚሊዮን ብር ፈጅቶ የቆመ ሲሆን ባለቤት አጥቶ ከቁጥር – 2 በባሰ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የአካባቢው የአመራር አካላት ገልፀዋል፡፡

ለመስኖ መሬት ውስጥ የሚቀበሩ ከቱርክ በውጭ ምንዛሪ የተገዙ ፕላስቲክነት ያላቸው በጣም ብዙ ቱቦዎች ለፀሐይና ዝናብ ተጋልጠው የሚበላሹበትን ጊዜ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡

ለዘጠኝ ዓመታት በሸንኮራ አገዳ የለማው መሬት 13,147 ሄክታር እና የተፈጠረው የስራ ዕድልም በአሁኑ ሰዓት 3,525 ብቻ እንደሆነ የቀረበው ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ግን ከዚህ ለም መሬት ትርፍ አምራች የነበረ 4,310 አባወራና እማወራ በህዝብ ብዛት 19,310 ሰው ለእንስሳትም ሆነ ለእርሻ የማይመችና በቂ ያልሆነ መሬት ላይ ሰፍሮ ተመፅዋች ሆኖ ከግለሰቦችና ከመንግስት ዕርዳታ እየተሰፈረለት እንደሆነ ነው የጃዊ ወረዳና የአዊ ዞን የአስተዳደር አካላት ያረጋገጡት፡፡ እንግልቱ የበዛበትና በፕሮጀክቱ መዘገየት ተስፋ መቁረጥ የጀመረው ማህበረሰብ 59.75 ሄክታር አገዳ በከብት እና 1,216.30 ሄክታር አገዳ በእሳት እንዲወድም ምክንያት መሆኑ በሪፖርት ቀርቧል፡፡

የአስተዳደር አካላቱ ፕሮጀክቱ ከልማት ተነሺዎች አልፎ በሌላ ወረዳ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ላይ ጭምር ተፅዕኖ ማሳደሩን በዝርዝር ለኮሚቴው አባላት አስረድተዋል፡፡

መንግስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ይልቅ ጅምር ላይ እንዲጠናቀቁ በጀት እንደሚመድብ ያስቀመጠው አቅጣጫ በዚሀ ፕሮጀክት ላይ እንዲተገበርና በድህነት ውስጥ ለወደቁ አርሶ አደሮች የድህነት መውጫ ፓኬጅ እንዲዘጋጅላቸው እነዚህ የአመራር አካላት ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የቡድኑ መሪ የተከበሩ አቶ አባቡ ብርሌ፤ በበለስ ቁጥር – 2 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ቦታ የተፈጠረው የሀብት ብክነት ያሳሰባቸው መሆኑን አመልክተው በፋብሪካው ዕጣ ፈንታ ላይ የተጀመረው ጥናት ቶሎ አልቆ ፋብሪካው ለባለሀብት ስለሚሸጥበት ወይም ለመንግስት አካል ተላልፎ ስለሚሰጥበት ጉዳይ ውሳኔ በፍጥነት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ ኮሚቴውም ጉዳዩን በፅሑፍም ሆነ በአካል ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ሪፖርት በማቅረብ አፈፃፀሙን እንደሚከታተልም አረጋግጠዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በበርካታ ችግሮች የተሳሰረ ቢሆንም ለመስኖ የሚሆን ውሃ ከበለስ ወንዝ ተጠልፎ የቀረበለትና ከኮሶበር እስከ ፕሮጀክቱ ድረስ 150 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ የተሰራለት ነው፡፡(ምንጭ፡-የህ/ተ/ም/ቤት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top