Connect with us

ከ30 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚመረምር ሳይንሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

ከ30 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚመረምር ሳይንሳዊ ጉባኤ በአዲስአበባ እየተካሄደ ነው

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ከ30 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚመረምር ሳይንሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

ኢትዮጵያ በ2050 ግዙፍ ተግዳሮቶችና ዕድሎች በሚል ርዕስ በአዲስአበባ ስካይላይት ሆቴል ዓለም አቀፍ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።

ዛሬ እና ነገ በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በኋላ የህዝቧ ቁጥር ወደ 200 ሚልየን ይደርሳል ተብሎ በሚታሰብበት ወቅት አገራዊና ከዜጎች የእለት ተእለት አኗኗር ጋር ወሳኝነት ባለው ሁኔታ የሚቆራኙ አስር የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮችን አግባብነት ባለው መንገድ ለመምራት የሚያስችል የቅድመ ተግባራትና እነዚህኑ ለማከናወን የሚያስችሉ እድሎች ላይ መምከር ጀምሯል።

ጉባኤው በትኩረት ከሚመክርባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የምግብ ዋስትና፣ ጤና፣ በግዙፍ ደረጃ ከተሞችን የማልማት፣የረቀቁ ኢንደስትሪያዊ የማምረት ተግባራት፣ የሀይል አቅርቦትና ከባቢ የአየር ጉዳዮችን በማካተት የትምህርት ሥርዓትና ብቃት ያለው አምራች የሰው ሀይል ልማትን የሚመለከት ነው።

በእነዚህ ግዙፍ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያላቸው ባለሙያዎችና ሊቃውንት፣ ፈፃሚዎች፣ ምሁራንና ተመራማሪዎች ሀሳቦችን በማቅረብ ምክክር እያደረጉ ናቸው።

ይህን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያስተባበረው የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ፣ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር፣ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር፣ከኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር መሆኑ ታውቋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top