Connect with us

ሲመሽ የሚጠጣ ሳይሆን ሲመሽ ችግኝ የሚያጠጣ እረፍት የለሽ መሪ ስላለን ታድለናል

Photo: Facebook

ጥበብና ባህል

ሲመሽ የሚጠጣ ሳይሆን ሲመሽ ችግኝ የሚያጠጣ እረፍት የለሽ መሪ ስላለን ታድለናል

ሲመሽ የሚጠጣ ሳይሆን ሲመሽ ችግኝ የሚያጠጣ እረፍት የለሽ መሪ ስላለን ታድለናል፡፡
የእርሻ መሬት ከሚነጥቅ ሥርዓት የገበሬ ማሳ ወደሚያጭድ መሪ ተሸጋግረናል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ስለምንፈልግዎት እያረፉ፡፡ | ከሰለሞን ሃይሉ በድሬቲዩብ

አራት ኪሎ ገብቶ እንደ ወዛደር መስራት፣ እንደቅጥረኛ መሮጥ፣ አልሞላ እንዳለው ሰው መዛበዝ መረገም ሳይሆን ጸጋ ነው፡፡ የደሃ ሀገር መሪ መሆናቸውን ያወቁት ጠቅላያችን የአንድ ደሃ ኑሮን እየኖሯት ነው፡፡ ይባትላሉ፡፡ ቀዳዳው በዝቶ እንጂ አንዱን ደካማ ሚኒስትር ቦታው ተክተው ቢሰሩለትም በወደዱ፤

ዶክተር አብይ ኩፍስ አይደሉም፡፡ ቀላልና ህዝቡን መሳይ ኑሮ መኖርን እንደሚመርጡ ከዕለት ውሎዋቸው መረዳት ይቻላል፡፡ ኤርትራ ከርመው ሲመጡ ከወዲ አፎም የተማረኩበት ቀለል ያለ ኑሮ መኖሩን ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ሹም ሲባል ትዝ የሚላቸው ሲመሽ የሚጠጣ ነው፡፡ ሲመሽ የሚጠጣ ባላባት ሲመሽ የሚጠጣ አብዮተኛ ተካ፣ ከዚያም ሲመሽ የሚጠጡ ታጋዮች መጡ፡፡ ምሽቱን ሲጠጡ ማምሸት የሹመት መለኪያው ሆነ፡፡ ባለሃብቱ ኦፊስ ባርና ሂልተን ጎራ ብሎ ከአራት በኋላ መመሪያ እያስጣሰ ጥቅሙን ሲያስጠብቅ የኖረው በምሽት ጠጪዎች ደካማ ጎን ተጠቅሞ ነው፡፡

አሁን ሌላ መሪ አገኘን፡፡ በዚህ ልክ ከሰፈርነው መስፈሪያውን የሚያልፍ ገደፍ የሚሞላ መሪ ነው ዶክተር አብይ አህመድ፡፡ ጠቅላያችን ሲመሽ የተከለውን ችግኝ ውሃ ያጠጣል፡፡ ራሱ እየነዳ መንደር ለመንደር ዞሮ፡፡ እንዲህ ያለ ካቢኔ አልገጠመውም፡፡ ቢሮውን ከፍቶ የማይገባው ሚኒስትር ብዙ ነው፡፡ እንኳን መንደር ሊዞር የመስሪያ ቤት ቅጥሩን የማያውቅ ሚኒስትር ባለበት ሀገር እንዲህ ያለ መሪ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡

ከዚህ ቀደም መሪዎቻችን ዓይናቸው የገበሬ መሬት ላይ ነው፡፡ ስንቱን ጎበዝ ገበሬ ለማኝ አድርገውታል፡፡ መሬቱን ባዩ ቁጥር ነጥቀው በማይረባ ካሳ መሬት አልባ አድርገውታል፡፡ የጤፍ እርሻን አበባ እርሻ ያደረጉ የተፈጥሮ ጠላቶች ዛሬ የሉም በእነሱ ምትክ የገበሬውን ጤፍ የሚያጭድ ደግ መሪ አይተናል፡፡ ማነው እስቲ ማሳ ውሎ ለጉራስ ጤፍ ያጨደ? ለጉራስ ወንዱ ሴት ላይ ተለጥፎ ፎቶ ይነሳል እንጂ መች ማጭድ ያነግባል?

የዶክተር አብይ ድንቅ ችሎታ ትጋትና ብርታት ነው፡፡ ስንፍናን የሚጠየፍ መሪ ስለሆነ ኦስሎ አድሮ፣ ኢዩቤልዩ እራት በልቶ ደንበል ችግኝ ውሃ የሚያጠጣ ጎበዝ የሀገሬን ገበሬ ኑሮ እየኖራት ነው፡፡ መሪውን የሚመስል ህዝብ ቢኖረን መልካም ነው፡፡ የክልል መሪዎች በጥቁር ቪ ኤይት ከመክነፍ እንዲህ ወርደው ከተሞቻቸውን ቢመለከቱ ለውጥ ይመጣል፡፡ የዶክተር አባይ እረፍት የለሽ ድካም እንደዜጋ ያሳስበናል፡፡ እያረፉ ቢሆን መልካም ነው፤፤ እናም እንዲህ እንበላቸው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እያረፉ፤ ምክንያቱም እንፈልግዎታለን፡፡

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top