Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቀበሉት ሽልማት ኢትዮጵያ ስትከበር አይተናል … ታዋቂ ሰዎች

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቀበሉት ሽልማት ኢትዮጵያ ስትከበር አይተናል … ታዋቂ ሰዎች
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቀበሉት ሽልማት ኢትዮጵያ ስትከበር አይተናል … ታዋቂ ሰዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ባሸነፉት የኖቤል የሠላም ሽልማት ኢትዮጵያ ስትከበር አይተናል ሲሉ ዶክተር ወዳጄነህ መሃረነ እና አርቲስት ስለሺ ደምሴ /ጋሽ አበራ ሞላ/ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለኖቤል የሠላም ሽልማት የበቁት ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በአገራቸው ለውጥ ለማምጣት እየወሰዷቸው ባሉ እርምጃዎች፤ በተለይም ከኤርትራ ጋር ሠላም ለማውረድ ባደረጉት ጥረት ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ተሸላሚ መሆን ለአገሪቷ ወጣቶች ምን አንድምታ አለው ሲል ኢዜአ ከታዋቂ ሰዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።

አስተያየታቸውን የሰጡት ዶክተር ወዳጄነህ መሃረነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትንሿ የገጠር መንደር በሻሻ ወጥተው በዓለም መድረክ ለዚህ ክብር መብቃታቸውን ወጣቶች እንደ አርዓያ ሊወስዱት ይገባል ይላሉ።

‘ሽልማቱ የፖለቲካ አመለካከት ጉዳይ አይደለም’ ያሉት ዶክተር ወዳጄነህ አገራዊ ጉዳይና ክብርም ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቀበሉት ሽልማት ‘እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያ ስትከበር አይተናል’ ነው ያሉት።

አርቲስት ስለሺ ደምሴ /ጋሽ አበራ ሞላ/ በበኩሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ ክብር መብቃት በከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች የበለጠ እንዲሰሩ የሚያበረታታ እንደሆነ ተናግሯል።

ወጣት ሲባል በቁመትና በዕድሜ ማደግ ብቻ ሳይሆን እውቀት ይዞ በመሆኑ ወጣቶች ከሌሎች አገራት ጋር የሚወዳደር እውቀት በመያዝ አገራቸውን ማበልፀግ እንደሚገባቸውም አስገንዝቧል።

ዶክተር ወዳጄነህም የበለፀገች ኢትዮጵያ እውን እንድትሆን ወጣቶች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ በመቆጠብ ትምህርትና ስራ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ነው ያሉት።

ወጣቶች ደሃ ነን ብለው በገንዘብ ልኬት አገራቸውን መለካት እንደሌለባቸው የገለፀው አርቲስት ስለሺ፤ የታሪክን ልኬት በማየት ለአገር አንድነት የተከፈለውን መስዋዕትነት በመገንዘብ አገራቸውን በእውቀት ማበልፀግ እንደሚገባቸው ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ደሃ ባለመሆኗ ያሏትን የተፈጥሮ፣ የባሕል እንዲሁም እንደ አገር ለመቆም የተከፈለውን መስዋዕትነት በመገንዘብ ‘የአስተሳሰብ ድህነትን በመፍታት የበለፀገች ኢትዮጵያን እንፍጠር’ ነው ያሉት።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top