Connect with us

ዩኔስኮም ለጥምቀት ያልኾነ መዝገብ ይቀዳደድ ብሎ ዓለም ቅርስ አድርጎታል

ዩኔስኮም ለጥምቀት ያልኾነ መዝገብ ይቀዳደድ ብሎ ዓለም ቅርስ አድርጎታል

ባህልና ታሪክ

ዩኔስኮም ለጥምቀት ያልኾነ መዝገብ ይቀዳደድ ብሎ ዓለም ቅርስ አድርጎታል

ዩኔስኮም ለጥምቀት ያልኾነ መዝገብ ይቀዳደድ ብሎ ዓለም ቅርስ አድርጎታል … ጥምቀት ከማዕዘን እስከ ማዕዘን ድንቅ

የሚታይበት የሀገር እሴት፤ በኮሎምቢያ ቦጎታ ስብሰባውን እያደረገ ያለው የዩኔስኮ የቅርስ ኮሚቴ ጥምቀትን በዓለም ቅርስ መዝገብ በማይዳሰስ ቅርስ ወካይ የሰው ልጆች መዝገብ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ዩኔስኮም ለጥምቀት ያልኾነ መዝገብ ይቀዳደድ ብሎ የዓለም ቅርስ አድርጎታል ይለናል በተከታዩ ዘገባው፡፡ | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

እርግጥ ነው እኛ ለእነሱ ብለን አይደለም ታቦታቱን አጅበን ጥምቀተ ባህር የወረድነው፡፡ ዓለም እኛን ከማወቁ በፊት እኛ ዓለምን የምናውቅ ህዝቦች ነን፡፡ እናም ዓለም ሊያውቀን መጣ፡፡ ሲያውቀን ገረመው፡፡ ዓለም እንዲገረም አንዳችም ድራማ የሰሩ አባቶች የሉንም፡፡ ይልቁንም በትህትና ያጎነብሳሉ፡፡ ይልቁንም በዝምታ ምስጢር ያኖራሉ፡፡ ምስጢር ሆና በኖረችው ሀገር የኖረው ድንቅ የጥምቀት ሥነ ሥርዓት የሰው ልጆች ሁሉ ወካይ ኾኖ በዓለም ቅርስ ተመዘገበ፡፡

እንዲመዘገብ አልነበረም አክሱም ወደ ንግሥቲቷ ማደሪያ ታቦታቱን አጅበን ማርያም እናታችን እያልን የወረድነው፤ እንዲመዘገብ አልነበረም በላሊበላ በታቦታቱ ፊት በቀይ ጥንግ ድርብ ያሬዳዊ ዜማን ያሰማነው፡፡ ዩኔስኮን በማሰብ አልነበረም ወደ ዐፄ ፋሲል ጥምቀተ ባህር ሎጋው ሽቦ ብለን ታቦት እንደሙሽራ ያጀብነው፡፡ ዓለምን ለመሳብ አልነበረም ኢራንቡቲ በወት ግባ ብለን አርባ አራት ታቦት ያነገስነው፡፡ ዩኔስኮ እንዲማልል አስበን መች ጋዲሎ ሜዳ ታቦት አነገስን? መች ባሮ ወንዝ ሆ እያልን ወረድን? መች የጋርዱላ ሰማይ ስር በፊላ ለታቦቱ ዘመርን? መች ከጦሳ ተራራ በታች እንዲህ ያለ ዜማ ዳር እስከዳር አሰማን?

ይሄን ሁሉ ያደርግነው ፈጣሪ እንዲሰማን ነበር፡፡ ለፈጣሪ ክብር በአባቶቻችን ያነገስነው ታቦት ዓለም ፊት አስከበረን፡፡

ጥምቀት ኢትዮጵያ በየማዕዘኑ ራሷን የምትገልጥበት እሴት ነው፡፡ ሀገር ልዩ ቀለም ለብሳ በልዩ ፍቅር መንፈሳዊ ሥርዓት የምትከወንበት ነው፡፡ እናቶቻችን ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ሲሉ ጥምቀት ከሁሉ እንዲቀድም ነገሩን፡፡

ዩኔስኮ ከእናቶቻችን ብሂል ሰማ፡፡ ለጥምቀት ያልሆነ መዝገብ ይቀዳደድ ብሎ ጥምቀትን በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ ወካይ የሰው ልጅ ሲል የዓለም ቅርስ አደረገው፡፡

ዩኔስኮ የጥምቀት በዓልን በዓለም አቀፍ ቅርስነት መዘገበ

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በእየዓመቱ ጥር 11 ቀን የሚከበረውን የጥምቀት በዓል በዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት እንደመዘገበው ትላንት ታህሳስ 1ቀን 2012 ዓ.ም ዕለት ገልጷል።ድርጅቱ ይህንን ውሳኔ ያደረገው በኮሎምቢያ፣ቦጎታ እያካሄደ ባለው ስብሰባው ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካሏት ሁለት ዓመታዊ ክብረ በአሏች ውስጥ ከእዚህ በፊት መስቀል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል።

UNESCO decided to inscribe TIMKET on the List of the Intangible Cultural Heritage of Humanity.Ethiopian Epiphany is a colorful festival celebrated all over Ethiopia to commemorate the baptism of Jesus Christ. The commemoration starts on the eve of the main festival, when people escort their parish church TABOT, a representation of the Tables of the Law, to a pool, river or artificial reservoir. Celebrants then attend night-long prayers and hymn services, before taking part in the actual festival the following day, when each TABOT is transported back to its church. The Ethiopian Epiphany is a religious and cultural festival whose viability is ensured through continuous practice and the pivotal contribution of the Orthodox clergy.

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top