Connect with us

ውፍረት መቀነስ የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በ37 በመቶ ለመቀነስ ይረዳል – ጥናት

ውፍረት መቀነስ የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በ37 በመቶ ለመቀነስ ይረዳል – ጥናት
Photo: Facebook

ጤና

ውፍረት መቀነስ የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በ37 በመቶ ለመቀነስ ይረዳል – ጥናት

ውፍረትን መቀነስ አይነት 2 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን በ37 በመቶ ለመቀነስ እንደሚረዳ አንድ ጥናት አመላከተ።

በአሜሪካ የተደረገው ጥናት ውፍረታቸውን የሚቀንሱ ሰዎች ለአይነት 2 የስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ያመላክታል።

ሰሞኑን ይፋ የሆነው እና በዘርፍ ባለሙያዎች በአሜሪካ የተደረገው ጥናት ለከፍተኛ ውፍረት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ያካተተ ነው።

በዳሰሳ ጥናቱ የሰዎቹ አኗኗር፣ አመጋገብ ሁኔታ፣ የቤተሰብ ታሪክ እና መሰል ጉዳዮች ታይተውበታል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በተመረጡ ሰዎች ላይ በተደረገው ጥናት አመጋገባቸውን በማስተካከልና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ውፍረት የቀነሱ ሰዎች ለአይነት 2 የስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ሆኗል።

የጥናት ቡድኑ እንደገለጸው በዚህ ሂደት ውፍረት የቀነሱ ሰዎች ውፍረት ካልቀነሱት አንጻር ሲታይ፥ ለአይነት 2 የስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው በ37 በመቶ ይቀንሳል።

ከዚህ ባለፈም ቤተሰቦቻቸው በዚህ በሽታ ተጠቂ ሆነው ከልክ በላይ ለሆነ ውፍረት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ውፍረታቸውን መቀነስ ከቻሉ ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸውን በ21 በመቶ ይቀንሳሉም ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ዩናይት ፕረስ ኢንተርናሽናል

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top