Connect with us

የአውሮጳ ሕብረት የደኅንነት ማስጠንቀቂያ!

የአውሮጳ ሕብረት የደኅንነት ማስጠንቀቂያ!
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የአውሮጳ ሕብረት የደኅንነት ማስጠንቀቂያ!

የአውሮጳ ሕብረት የደኅንነት ማስጠንቀቂያ! (በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን)

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ170 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ የሚለው ዜና ከሰሞነኛ ጉዳዮቻችን አንዱ ነው፡፡ ከምዕራቡ ዓለም ኃይሎች ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ የኢትዮጵያ አጋር ሆኖ የሚነሳው የአውሮጳ ሕብረት ነው፡፡ በአጠቃለይ ለአፍሪቃ ቀንድም የልማት፣ የሠላምና ፀጥታ አጋር ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ሶማሊያ ሠላም ለማስፈን የገባው የአሚሶም ሠራዊት እስካሁን የቆመው በዚሁ ሕብረት ድጋፍ ነው፡፡

የዚህ ሕብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ደቪድ ኮርፔላ ለአለቆቻቸው የአካባቢውን ሠላምና ፀጥታ በሚመለከት ያላቸውን ትንተና አቅርበዋል፡፡ የሪፖርቱ ግልባጭ የኢትዮጵያ መንግሥት ደርሶት ስለመሆኑ አላረጋገጥሁም፡፡ ኢትዮጵያን በሚመለከት አምስት ነጥቦችን ያካተተው የደቪድ ሪፖርት ደርሶኛል፡፡እንደሚከተለው ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ፡፡

1ኛ-የአውሮጳ ሕብረት ኢትዮጵያ የገጠማትን አስቸጋሪ ፈተና በጥንቃቄ እየተከታተለ ነው፡፡ የአገሪቱ አመራር አገሪቱን ወደ መቀመቅ እያወረዳት (the leadership is taking the country down the drain) ነው፡፡

2ኛ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደመጀመሪያው ተቀባይነቱ ለመመለስ ከፈለገ ወደ ኦሮሞ ደጋፊዎቹና መራጮቹ (Constituency) መመለስ አለበት፡፡ ይህ አመራር በአገር ውስጥም በውጭም በጥንቃቄ መታየት ያለበት ነው፡፡ ዓለማቀፍ ዕውቅናውን (የኖቤል ተቀባይነት) ተጠቅሞ ውስጣዊ ቅቡልነት ለማምጣት የሚፈልግ አመራር ነው-ያለው፡፡ይሁን እንጂ እንዳሰበው አልሄደለትም፡፡ በሽልማቱ ማግስት በኦሮሚያ ውስጥ እርሱን የሚቃወም አመጽ ተካሄደ፤‹መደመር› የተሰኘው መጽሐፉም ተቃጠለ፡፡ይህ ደግሞ ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይን ግላዊ በደል እንደደረሰበት እንዲያስብ አድርጎታል፡፡

ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሁን አብረውት ያሉት የአዴፓ አጋሮቹ ናቸው፡፡ይሁን እንጂ ወደ ኦሮሚያ ተመልሶ ደጋፊዎቹንና መራጮቹን (Constituency) ይዞ ካልመጣ፣መጨረሻ ላይ አዴፓዎችም ይተውታል፡፡

3ኛ-ዐቢይ እየተጓዘ ያለው ከውጭ ያገኘውን ተቀባይነትና ዕውቅና መከታ አድርጎ ነው፡፡ይህ ደግሞ ለአገሪቱ ብዙም አይጠቅምም፡፡በኢትዮጵያ ልሂቃን ውስጥ በአሁኑ ወቅት አንድ አሳማኝ ስጋት አለ፡፡ይኸውም ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አገሪቱን ወደ ቀውስ ይዘዋት ይሄዱ ይሆን የሚል ነው፡፡የሚነገረውን ነገር ወደጎን ብሎ እርምጃ መውሰድ ካልቻለና መፍትሔ ማቅረብን ችላ ካለው አገሪቱ ውስጥ አደገኛ ሁኔታ እንደሚፈጠር ማንም አይጠራጠርም፡፡ያኔ ማንም አጠገቡ አይኖርም፤ኖቤል የሸለሙት ኖርጂያንም ጭምር!

4ኛ-ሕብረቱ የአገሪቱን ጉዳይ በአጽንኦት እየተከታተልን ነው፡፡ኢትዮጵያ ለአካባቢው ሠላምና ፀጥታ ዋነኛ ተዋናይ የነበረች አገር ብትሆን አሁን በመፍረስ ስጋት ውስጥ ያለች ሆናለች፡፡ይህ እንዳይሆን ኢትዮጵያዊያን ፖለቲካቸውን ማስተካከል አለባቸው፡፡

5ኛ-የሚመጣው ምርጫ ወሳኝ ነው፡፡በተለይም ቅቡልነት ያለው መንግሥት ወደ ሥልጣን እንዲመጣ ወይም አሁን ያለው መንግሥት በሕዝብ የሚወደድ መሆኑ የሚፈተሸበት አጋጣሚ ነው፡፡ሀቀኛ ጥረትና ዝግጅት የሚደረግበት ምርጫ ከሆነ ሕዝብ ያሸንፋል፡፡ምርጫውን መሠረዝ ግን የበለጠ ቀውስ መፍጠር ነው፡፡በርግጥ እዚህ ጋር የጠቅላይሚኒስትሩ ይሁንታ ያስፈልጋል፡፡እርሳቸው ብወዳደር አሸንፋለሁ ወይስ አላሸንፍም ብለው አስበው በሚደርሱበት ቁምነገር ላይ ይወሰናል፡፡

እነዚህ ናቸው የልዩ መልዕክተኛው መልዕክቶች፡፡ስለ ሱዳን፣ኤርትራና ሱማሊያ የሚያትት ክፍልም አለው፡፡ኤርትራን ‹ማዕቀብ ተነስቶላትም ያልተሻሻለች አገር› ይላታል፡፡ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችው የሠላም ጉዞም የበለጠ ሥር እንዲሰድ የአውሮጳ ሕብረት ማገዝ እንዳለበት ይመክራል፡፡ሁለቱን አገራት በተለይ በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር ሕብረቱ መጣር እንዳለበት ይጠቁማል፡፡በሱዳንም የአውሮጳ ሕብረት ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠብቀው ይተነትናል፡፡በስም እየጠቀሰ ባለሥልጣናቱ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆኑ ያስረዳል፡፡

(ይህ ጽሁፍ በከፊል ባሳለፍነው ቅዳሜ ከታተመችው ፍትሕ መጽሔት የተወሰደ ነው)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top