Connect with us

ሩዋንዳ በመርፌ የሚሰጥ አዲስ የኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒትን ልትሞክር

ሩዋንዳ በመርፌ የሚሰጥ አዲስ የኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒትን ልትሞክር

ጤና

ሩዋንዳ በመርፌ የሚሰጥ አዲስ የኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒትን ልትሞክር

ሩዋንዳ ካሁን በፊት ከነበረው የተሻለና ዘላቂነት ያለው አገልግሎት የሚሰጥ በመርፌ የሚሰጥ የኤች አይ ቪ መድኃኒትን ልትሞክር እንደሆነ የሩዋንዳ ባዮሜዲካል ማእከል ገለፀ፡፡

የመድሃኒቱ ሙከራ ከተጠናቀቀ ና ውጤታማ ከሆነ አንድ የኤች አይ ቪ ታማሚ እንደ ከዚህ በፊቱ በየቀኑ መድሃኒቱን መውሰድ እንደማይጠበቅበት ተጠቅሷል፡፡

ዶክተር ሳቢን ንሳንዚማና እንደሚሉት በፊት የነበረው መድሃኒት በየቀኑ መውሰድ ግዴታ ሲሆን፤ የአሁኑ በመርፌ ሊሰጥ የታሰበው አዲሱ የኤች አይ ቪ ኤዲስ መድኃኒት ግን አንዴ ከተሰጠ ለስምንት ሳምንታት ያገለግላል።

ሙከራው ውጤታማ ከሆነ በሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ በፃታዊ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ላይ በማተኮር ለ20ኛ ጊዜ እአአ ከታህሳስ 1 እስከ 7 በሚካሄደው አለም አቀፍ ኮንፈርንስ ላይ ለውይይት እንደሚቀርብም ተገልጿል፡፡

እንደ ዶክተር ንሳንዚማና ኮንፈረንሱን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው ባላት መሰረተ ልማት፣ በጤና፣በደህንነት እና በኤች አይቪ ፕሮግራምና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ውጤታማ ሥራ በመስራቷ ነው።
በመድረኩም ከተለያዩ የአለም ሀገራት በኤች አይ ቪና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ዙርያ ጥናት ያካሄዱ ሰዎች ተገኝተው ሰፋ ያለ ሙያዊ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል ነው የተባለው።

የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት እንደሚያሳየው በሩዋንዳ እአአ ከ2010 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ የኤች አይቪ ስርጭት በ20% መቀነስ መቻሉ ና ከኤች አይቪ ኤዲስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሽታዎችም በ50 በመቶ መቀነሱን የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top