Connect with us

ሶዴፓ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ወሰነ

ሶዴፓ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ወሰነ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ሶዴፓ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ወሰነ

የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ የቀረበውን ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ ።

የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ ፓርቲው ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ ላይ እንደገለጹት የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀትና የኢህአዴግ ውህደት ሶዴፓ የቆመለትን የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው። ( ኢዜአ )

ቀደምስል:- 

ሶዴፓ ምን እያለን ነው?
(በኃይሉ ሚዴቅሳ ፍስሃጽዮን)

መቼም የኢሕአዴግ ውሕደት (በትክክለኛ የሕግ አጠራሩ መክሰም) ሰሞነኛ አጀንዳ ሆኗል፡፡ከጉለሌ እስከ ሞያሌ፣ከባሌ እስከ መቐለ ይሄ ጉዳይ መነጋገሪያ ነው፡፡የፓርቲው መዋኸድ በጣም ፈጥኖ እየሄደ ነው፡፡ይሄ ፓርቲ ተዋኸደ፣ተበታተነ፣ቀጠነ፣ተነነ ጉዳያችን መሆን አልነበረበትም፡፡ግን ከጫፍ ጫፍ አገሪቱን እርሱ መዋቅር ላይ የተንጠለጠለች አድርጎ ስለቀረፃት የእርሱ አንድ ነገር መሆን አገርን አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ነው-ሰዎች አጀንዳ ያደረጉት፡፡እንጂማ እኛ አገር ፓርቲ መዋኸድም ሆነ መፍረስ ብርቃችን አይደለም፡፡

በዚህ ውሕደት ላይ ዋነኛ ተዋናይ ሆነው በየ መድረኩ አስተያየት ሲሰጡና የውሕደቱን አስፈላጊነት ሲሰብኩ የነበሩት አንዳንድ ድርጅቶች አሁን ሸርተት ብለዋል፡፡ሕወሓት ላለፉት ዓመታት የውሕድ ፓርቲን አስፈላጊነት ስትሰብክ ኖራ፣አጀንዳው ጠረጴዛ ላይ ሲመጣ ‹‹እኛ 45 ሰዎች የሚሊዮኖችን ድርጅት ለማፍረስ ሕጋዊ ሥልጣን የለንም›› ብላ በማዕከላዊ ኮሚቴዋ በኩል ቀርታለች፡፡ይህ የኢሕአዴግ ውሳኔ ብዙ የሕግና የፖለቲካ ጥያቄዎች የተነሱበት ቢሆንም፣ቢያንስ ሱማሌ ክልልን የሚያስተዳድረው ሶዴፓ ይህንን ይቃወማል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር፡፡ይሁን እንጂ ለመዋኸድ 7 ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪና የፓርቲው ማዕላዊ ኮሚቴ አመራር ኢንጂነር ሞሐመድ ሻሌ ‹ማዕከላዊ ኮሚቴው ሶዴፓን የማክሰም ሥልጣን የለውም›› በማለት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡ይህ የሶዴፓ አቋም ከሕወሓት አቋም ጋር የተመሣሰለ ነው፡፡እንዲያም ሆኖ ድርጅቱ መዋሐድን በመርህ ደረጃ የተቀበለው ቢሆንም፣ሰባት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል፡፡

1ኛ- አሁን ያለው ፌደራል አደረጃጀትና ሥርዓት እንደማይሸራረፍ ማረጋገጫ ይሠጠን፡፡
2ኛ-በሕገ-መንግሥቱ የተሰጠን ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነትና የመወሰን መብት እንደማይነካ ዋስትና ይቅረብ፡፡
3ኛ- የሶማሊኛ ቋንቋ በክልላችን የአስተዳደርን የትምህርት ቋንቋ መሆኑ ላይ አንደራደርም፡፡
4ኛ-የሶማሊኛ ቋንቋ የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ ይሁን (ልክ እንደ አማርኛ፣ኦሮምኛ፣ትግርኛና ሌሎች)

5ኛ-አሁን ያለው የሶዴፓ መዋቅርና የአባላት አደረጃጀት አይነካም፡፡
6ኛ-የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም የክልላችንን ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ ስሪት ከግምት ውስጥ ያስገባ፡፡
7ኛ-በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የሚኖረን የሥልጣን ድርሻ የክልላችንን የቆዳ ስፋት ከግምት ውስጥ ያስገባ ይሁን!

እነዚህ ሳይሟሉ ወደ ውሕደት እንደማይገባ የተናገረው ፓርቲው ቀጣይ እጣፈንታው ምን እንደሚሆን ግን አላመላከተም፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top