Connect with us

የአንበጣ መንጋ በአምስት ክልሎች ተከስቷል፤ ግብርና ሚ/ር ተረጋጉ እያለ ነው

የአንበጣ መንጋ በአምስት ክልሎች ተሰስቷል፤ ግብርና ሚ/ር ተረጋጉ እያለ ነው
Photo: Facebook

ዜና

የአንበጣ መንጋ በአምስት ክልሎች ተከስቷል፤ ግብርና ሚ/ር ተረጋጉ እያለ ነው

ከመስከረም 2012 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አገራችን የገባውንና እየገባ የሚገኘውን የአንበጣ መንጋ ክስተት በቂ ቅድመ ዝግጅት ስራ የተሰራ በመሆኑ የከፋ ጉዳት እንዳያድርስ በመቆጣጠር ላይ ነው፡፡ ቁጥጥሩን ለማሳለጥ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አንበጣው በ5 ክልሎች እና በ1 ከተማ መስተዳድር በ62 የወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን በተደረገ የተቀናጀ የአሰሳና የቁጥጥር ስራ መረጃ መሰረት፡

 በአጠቃላይ እስከ ህዳር 10/2012 ዓ.ም የአንበጣ ክስተት መኖር አለመኖሩን አሰሳ የተደረገበት የመሬት ስፋት ድግግሞሽ ጨምሮ 93 ሺ 489 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ፡

 አንበጣ የተገኘበት የመሬት ስፋት 37,039 ሄ/ር ሲሆን
 አጠቃላይ መከላከል የተደረገት የመሬት ስፋት 30 ሺ 956 ሄ/ር ነው፡፡ የመከላከሉና የመቆጣጠሩ ስራ እየተካሄደ የሚገኘው

በአየርና በመሬት ነው፡፡ ይኻውም በአውሮፕላን፣ በተሽከርካሪ በተገጠመውና በሰው ታዝሎ በሚረጭ የመርጫ መሳሪያዎች በመጠቀም ጭምር ሲሆን በባህላዊ መንገድ ባረፈበት በመጨፍጨፍ ቁጥሩ የመቀነስ ስራዎች በስፋት ተሰርቷል፡፡
የፀረ-ተባይ ርጭት የተካሄደው መሬት ሽፋን፡

• በአውሮፕላን 10 ሺ 131 ሄ/ር መሬት የሚሸፍን ርጭት የተካሄደ ሲሆን
• በተለያዩ መርጫ መሳሪያዎች በመታገዝ 21ሺ 625 ነጥብ 75 ሄ/ር መሬት ላይ ፀረ-ተባይ ርጭት በማድረግ የመከላከል ስራ ተሰርቷል፡፡

ለዚህም ጥቅም ላይ የዋለ ፀረ-ተባይ ኬሚካል መጠን 10 ሺ 784 ነጥብ 51 ሊትር ነው፡፡
አጠቃላይ የበረሃ አንበጣ በተከሰተባቸው ክልሎች ለመከላከል ስራ የተደረገ ድጋፍና የተቀናጀ ርብርብ ስንመለከት

 ትንበያውን መሠረት በማድረግ አስቀድሞ ግንዛቤ መፍጠርና የመካለከያ ዘዴዎች ስልጠና እስከ ታች የሕ/ሰብ ክፍል መስጠትና ስካውት (አንበጣ መከሰት አለመከሰቱን በመለየት አሰሳ በመድረግ ሪፖርት የሚያደርጉ ባለሙያዎችና የሰለጠኑ ሰዎች) መቅጠር፣

 የፀረ-ተባይ አቅርቦት ዝግጅት 96 ሺ ሊትር ግዥ ተፈፅሟል፣

 ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር በስራ ላይ የተሰማሩ 26 የዘርፉ የቴክኒክ ባለሙያዎች እና 16 ተሽከርካሪዎች በየክልሉ ተገኝቶ እንዲሰሩና በቀጣይነት እንድደግፉ ተደርጎ እየተሰራ ይገኛሉ፡፡

ለዚህም ግብርና ሚኒስቴር የመከላከያና መርጫ መሳሪያዎች አቅርቦት አመቻችቶ እየሰራ ያለ ሲሆን
 4 አውሮፕላን የአንበጣ መንጋ ባለበት ርጭት እንዲያካሄድ ማመቻቸት ስራ ተሰርቷል፡፡
 8 ተሽከርካሪ ላይ የተጠመዱ መርጫ መሳሪያዎች፣
 ከ100 በላይ ባለሞተር መርጫ መሳሪያዎች፣
 በርካታ መርጫ መሳሪያዎች ለፀረ-ተባይ ርጭት ስራ ተሰማርተው የበረሃ አንበጣ በተከሰተባቸው ክልሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል፡፡

ይህን በማድረግ በተሰራው ስራ ከ95 በመቶ በላይ የመከላከል ስራ ተሰርቷል፡፡ አሁንም ያለው ትንበያና በመሬት እየተደረገው ያለው አሰሳ የሚያመለክተው ከየመን የሚገባ መንጋ እንዳለና ቀደም ብሎ የገባ መንጋ የጣለው እንቁላል የተፈለፈሉ ኩብኩባዎች እንዳለ የሚያመለክት ስለሆነ ህብረተሰቡ አሁን የተቀናጀ የመከላከል ስራ መስራት እንደሚገባ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top