Connect with us

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ተጀመረ

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ተጀመረ
Photo: Facebook

ዜና

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ተጀመረ

የሲዳማ ዞን በክልል የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው።

በሲዳማ ዞን ባሉ 1692 የምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ እየተሰጠ ነው፡፡

ጉዳዩን አስመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለውን የዴሞክራሲ ጎዳና አመላካች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዜጎች ድምጽ ለመስጠት በሚወጡበት በዛሬው ዕለት ሁሉም ተሳታፊዎች ለሂደቱ ሰላማዊነትና ዴሞክራሲያዊነት እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሃዋሳ ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች የኢዜአ ሪፖርተሮች ተዘዋውረው እንደተመለከቱት ህዝቡ ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ በየድምጽ መስጫ ጣቢዎያዎቹ ተሰልፏል። ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ሲሆንም ድምጽ መስጠት ተጀምሯል።

ከሃዋሳ ከተማ በ12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የቱላ የገጠር ከተማም ህዝቡ ከማለዳው ጀምሮ ድምጽ እየሰጠ ይገኛል።

የድምጽ አሰጣጡ ሂደትም ሰላማዊ መሆኑን ሪፖርተሮቹ ተመልክተዋል።

ለሲዳማ በክልል የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ድምጽ ሰጪዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አሰጣጥ ለመታዘብ በሃዋሳ ከ300 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በድምጽ መስጫው ዕለት ተቋማት ዝግ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመምከር ውሳኔ መተላለፉ አይዘነጋም።

በዚሁ መሰረት ዛሬ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ዝግ ናቸው።

ገበያዎችና የጫት ግብይት በሚካሄድባቸው ሥፍራዎች በዕለቱ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደማይኖር ቀደም ብሎ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top